የፕሪሚዬር ሊጉ የመክፈቻ ሳምንታት ጨዋታዎች በሀዋሳ እንደሚካሄዱ ተገለፀ

የፕሪሚዬር ሊጉ የመክፈቻ ሳምንታት ጨዋታዎች በሀዋሳ እንደሚካሄዱ ተገለፀ

የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የምድብ አንድ የመጀመሪያ ዘጠኝ ሳምንታት ጨዋታዎች በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄዱ ተገልጿል።

ቀደም ብሎ በወጣው መርሐግብር የፕሪሚዬር ሊጉ የመጀመሪያ ዘጠኝ ሳምንታት ውድድር በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ እንደሚደረግ መገለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ድሬዳዋ ከተማ ውድድሩን ለማስተናገድ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ በመሆኑና ዝግጁ አለመሆኑን በመግለፁ ድሬዳዋ ላይ ሊካሄዱ የነበሩ ጨዋታዎች ወደ ሀዋሳ ከተማ መዛወራቸውን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አሳውቋል።

አክሲዮን ማህበሩ አያይዞም የተስተካከለው የጨዋታ መርሐግብር በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ገልጿል።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ