የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ከ8 ሺህ 4 መቶ በላይ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታዉቋል።
አንዳንድ የአርባምንጭ ከተማ ነጋዴዎች፤ በህጋዊ መንገድ በተለያዩ የንግድ ስራዎች ላይ ተሰማርተው እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው ህጋዊነትን በመጣስ የሚሰሩ አንዳንድ ነጋዴዎች በሀገርና በህዝብ ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖዎች ከፍ ያለ እንደሆነ ተናግረዋል።
የሚስተዋለውን ህገወጥ ተግባር ለመከላከል በርካታ የቁጥጥር እና የክትትል ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ተናግረዋል።
ህጋዊ የንግድ ስርዓትን በመጣስ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩት ግለሰቦችና የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃዎች እንደተወሰዱ መሆኑን ኃላፊዋ ገልፀዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት የምርት አቅርቦት በማሳደግና የሰንበት ገበያዎችን በተጨማሪ በማቋቋም ለህብረተሰቡ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችንና የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የሚስተዋለውን የኑሮ ዉድነት ለማረጋጋት በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ ስምረት አስማማው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር በሀገሪቱ አንድነት እና ሠላም ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ