ክርስቲያኖ ሮናልዶ የክብር ሽልማት ተሰጠው
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የምንጊዜም ምርጡ ተጫዋች በመባል የክብር ሽልማት ተሰጥቶታል።
የአምስት ጊዜ የባሎንዲኦር አሸናፊው ሮናልዶ ይህ የክብር ሽልማት የተሰጠው ከፖርቹጋል እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሽልማቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት በርካታ ሽልማቶች ያሉት ቢሆንም ይሄኛው ሽልማት ግን የተለየ መሆኑን ተናግሯል።
የ40 ዓመቱ ተጫዋች ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን በ223 ጨዋታዎች 141 ጎሎችን በማስቆጠር በመላው ዓለም በብሔራዊ ደረጃ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ መሆኑ ይታወቃል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ “ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት!” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ክላስተር ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ አሠልጣኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ጀምሯል
”ያሆዴ” የአንድነት፣ የፍቅርና መተሰሳሰብ በዓል በደማቅ ስነስርዓት እየተከበረ ነው