አርብቶ አደሩ በሚያመርታቸው የግብርና ምርቶች ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መስከረም 25/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) አርብቶ አደሩ በሚያመርታቸው የግብርና ምርቶች ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊና መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምዕራፍ አንድ ማጠናቀቂያ መርሃግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር)፥ በዚህ ወቅት ለአርብቶ አደሩ የኑሮ መሰረቱ የግብርና ልማት ስራዎች መሆናቸውን ጠቁመው፥ አርብቶ አደሩ በሚያመርታቸው የግብርና ምርቶች ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
አርብቶ አደሩ በተለይ የሰዉ ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት አደጋዎችን መቋቋም የሚያስችሉ ተግባራት መጠናከር እንዳለባቸውም አስረድተዋል ።
የክልሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤካል ነትር መንግስት በቆላማ አካባቢ ለሚኖሩ ህብረተሰብ ክፍሎች ለኑሮ መሻሻል የተለያዩ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል ።
በክልሉ ባለፉት ጊዜያት የአርብቶአደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የኑሮ ማሻሻያ የልማት ፕሮግራሞች ተግባራዊ ስለመደረጋቸው አቶ ኤካል ጠቁመዋል ።
ተቋሙ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰራ ነው ብለዋል።
በዚህም ከ198 ሺህ በላይ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በቀጥታ ተጠቃሚ መሆናቸውን የቢሮ ኃላፊ አስረድተዋል ።
በመረሃ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ “ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት!” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ክላስተር ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ አሠልጣኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ጀምሯል
”ያሆዴ” የአንድነት፣ የፍቅርና መተሰሳሰብ በዓል በደማቅ ስነስርዓት እየተከበረ ነው