አሰልጣኝ ስቴቨን ጄራርድ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ በንግግር ላይ ነው

አሰልጣኝ ስቴቨን ጄራርድ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ በንግግር ላይ ነው

እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ስቴቨን ጄራርድ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሬንጀርስ ለመመለስ ንግግር ማድረግ መጀመሩ ተገልጿል።

የስኮትላንዱ ክለብ ከቀናት በፊት ዋና አሰልጣኙን ሩዜል ማርቲንን ከሀላፊነት ማሰናበቱ ይታወሳል።

አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው ክለቡ የቀድሞ የሊቨርፑል ታሪካዊውን ተጫዋች ስቴቨን ጄራርድን በድጋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ሁለቱ አካላት ንግግር ማድረግ መጀመራቸውን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።

የ45 ዓመቱ አሰልጣኝ ከዚህ ቀደም የግላስኮውን ክለብ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2018 እስከ 2021 ድረስ በሀላፊነት መምራቱ ይታወሳል።

በቆይታውም በሴልቲክ የበላይነት ተይዞ በሚገኘው የስኮቲሽ ፕሪሚየር ሺፕ በባላንጣቸው ጣልቃ በመግባት በ2021 የሊጉን በጄራርድ መሪነት ማንሳቱ ይታወቃል።

በመቀጠል በእንግሊዙ ክለብ አስቶንቪላ እና በሳውዲ ክለብ አል ኤቲፋቅ ያልተሳካ የማሰልጠን ጊዜን አሳልፏል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ