በ5000 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ 3 ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለፍፃሜ ደረሱ

በ5000 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ 3 ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለፍፃሜ ደረሱ

በቶኪዮ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣ መዲና ኢሳ እና ፋንታዬ በላይነህ ለፍፃሜ ደርሰዋል።

በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለችው አትሌት ፋንታዬ በላይነህ ውድድሯን 6ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ወደ ፍፃሜ አልፋለች።

እዚሁ ምድብ ላይ የማጣሪያ ውድድሯን ያከናወነችው አትሌት ብርቄ ሃየሎም 9ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ቀጣዩ ዙር አላለፈችም።

በሁለተኛው ምድብ የማጣሪያ ውድድራቸውን ያከናወኑት አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና መዲና ኢሳ አብረው ወደ ፍፃሜው ተሻግረዋል።

ምድቡን ጉዳፍ ፀጋዬ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ መዲና ኢሳ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ29 ደቂቃ ላይ የሚካሄድ ይሆናል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ