ስፔን ከ11 ዓመታት በኋላ የቀዳሚነቱን ቦታ ያዘች
ሀዋሳ፡ መስከረም 08/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ወርሃዊ የፊፋ የዓለም ሀገራት ደረጃ በዛሬው ዕለት ይፋ ሲደረግ አውሮፓዊቷ ሀገር ስፔን የቀዳሚነቱን ቦታ ከወቅቱ የዓለም ዋንጫ ባለክብሯ አርጄንቲና ተረክባለች።
ላሮጃዎቹ በመስከረም ወር ውስጥ ባከናወኗቸው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ሁለቱንም ማሸነፍ መቻሏ ደረጃዋን እንድታሻሽል ረድቷታል።
ለበርካታ ወራት የዓለም ቁጥር 1 ደረጃን ይዛ የቆየችው አርጄንቲና በዚህ ወር በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው በኢኳዶር መሸነፏ በሁለት ደረጃዎች እንዳታሽቆለቁል አድርጓታል።
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን 2ኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዓለም 147ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ከዓለም 11ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ነች።
ዘጋቢ: ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የአንደኛ ደረጃ አትሌትክስ አሰልጣኞች ተመረቁ
ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን የክለቡ ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ለማስፈረም ተስማማ
ሶስቱ ብቸኛ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች