አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ወደ ቤኔፊካ
ከቀናት በፊት ከቱርኩ ክለብ ፌኔርባቼ አሰልጣኝነት የተሰናበቱት ጆዜ ሞሪኖ ቤኔፊካን በዋና አሰልጣኝነት ለመረከብ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
የፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ ትናንት ምሸት በሻምፒዮንስ ሊጉ ከ2ለ0 መምራት ተነስቶ 3ለ2 ከተሸነፈ በኋላ አሰልጣኝ ብሩኖ ላዥን ከሃላፊነታቸው አሰናብቷል።
በዚህ መነሻ ቤኔፊካ ከ19 ቀናት በፊት ከሀላፊነት የተነሱትን አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖን ለመሾም ተስማምቷል።
በአውሮፓ በርካታ ክለቦችን ማሰልጠን ያቻሉት ሞሪኖ ከ21 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገራቸው ሊግ የሚመለሱ ይሆናል።
ጆዜ ሞሪኖ ቤኔፊካን የሚይዙ ከሆነ ከ13 ቀናት በኋላ የቀድሞ ክለባቸው ቼልሲን በሻምፒዮንስ ሊጉ ይገጥማሉ።
ዘጋቢ: ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ከ29 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙት ኢትዮጵያ እና ሴኔጋል
ሳዲዮ ማኔ በትውልድ መንደሩ ባምባሊ 20 ሚሊዮን ዶላር በመመደብ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክት ጀመረ
ካይ ሃቨርትዝ ጉዳት አጋጠመው