በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ምሁር-አክሊል ወረዳ በመንግስትና በህብረተሰቡ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ምሁር-አክሊል ወረዳ በመንግስትና በህብረተሰቡ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ሕዳር 06/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ምሁር-አክሊል ወረዳ በመንግስትና በህብረተሰቡ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎች የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

‎አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በጎ አድራጎት ድርጅት በ26 ሚሊዮን በጀት ያስገነባቸው የሐዋሪያት የመጀመሪያ ደረጃና መካከለኛ ትምህርት ቤት እና በ20 ሚሊየን ብር ወጪ የሐዋሪያት ወደ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሸጋገረው ልማት ሥራዎች ይጠቀሳሉ።

‎የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ፣ አምባሳደር ምሰጋናዉ አረጋ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ደቸ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ጨምሮ የተለያዩ የሀገር ዉስጥና የዉጪ እንግዶች በምረቃዉ ሥነ-ሥርዓት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ወ/ማሪያም