ለትውልድ ግንባታ መሠረት ለሆነው የሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ ሕዳር 06/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለትውልድ ግንባታ መሠረት ለሆነው የሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) አሳሰቡ፡፡
“አገር በትውልድ፤ ትውልድ በትምህርት ይገነባል” በሚል መሪ ቃል 2ኛ ዙር የትምህርት አስተዳደር ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የትምህርት ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል።
በየትምህርት ቤቶች የትምህርት ግብኣት ማሟላት፣ ትምህርት ቤቶችን ምቹ ማድረግ፣ የመምህራን አቅም ግንባታ ሥልጠናን ማጠናከርና ጥቅማ ጥቅም ማስጠበቅ ላይ እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።
ስለሆነም ለዘርፉ ውጤታማነት የወላጅ ተገቢ ድጋፍና ክትትል ለተማሪው ውጤት መሻሻል የላቅ ድርሻ እንደሚያበረክትም ገልጸዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በበኩላቸው፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በትምህርት ሴክተር በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን ተናግረዋል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረው ትምህርት ለትውልድ መርሃ-ግብር ከ1 ቢሊዮን 118 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በጥሬና በገንዘብ ሲተመን ተሰብስቦ ከ3 ሺህ 8 መቶ 57 የትምህርት ቤቶችን ማስገንባትና ማስጠገን መቻሉን ተናግረዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንሼቲቭ በሆነው የሞዴል ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ከ1 መቶ 85 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከ40 በላይ ትምህርት ቤቶች በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ሲሆን 26 የሞዴል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውንም ገልፀዋል።
በ2ኛ ዙር የትምህርት አስተዳደር ጉባዔ በክልሉ ከ5 መቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ከ10 ሺህ እስከ 1 መቶ ሺህ ብር ድረስ የተሸለሙ ሲሆን ለትምህርት ዘርፍ ውጤታማነት የድርሻቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱት ግለሰቦች፣ ተቋማትንና የባለድርሻ አካላት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚወጡ ተመራቂ ሰልጣኞች በሰለጠኑበት ዘርፍ ሀገሪቱ ለጀመረችው የብልጽግና ጉዞ የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ምሁር-አክሊል ወረዳ በመንግስትና በህብረተሰቡ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው
ክህሎት መር ስልጠና በመተግበር በሀገሪቱ ያለውን ፀጋ ተጠቅሞ በትጋት ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ