ማንቸስተር ሲቲ የፊል ፎደን ውል ለማራዘም ስራ መጀመሩ ተገለፀ
የእንግሊዙ ክለብ ማንቸስተር ሲቲ የወሳኙን ተጫዋች ፊል ፎደንን ኮንትራት ለማራዘም ስራ መጀመሩ ተገልጿል።
ከክለቡ አካዳሚ የተገኘው ፎደን በአሁኑ ሰዓት ከሲቲዝኖቹ ጋር ያለው ውል ከሁለት ዓመት በኋላ ይጠናቀቃል።
በዚህ ዓመት የቀደመ ብቃቱን መልሶ ያገኘ በሚመስለው የ25 ተጫዋች ብቃት ደስተኛ የሆኑት የክለቡ አመራሮች ውሉን ለማራዘም እየሰሩ መሆኑ ተዘግቧል።
ከመጋቢት ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የቀረበለት ፎደን በክለቡ ለመቆየት የሚያደርገው ድርድር በስምምነት እንደሚቋጭ ተስፋ ተጥሎበታል።
ድርድሩ በስምምነት የሚቋጭ ከሆነ በኤቲሐድ እስከ 2030 ድረስ የሚያቆየውን የ5 ዓመት ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ዎልቭስ ሮብ ኤድዋርድስን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ቤንች ቡና ማጂ፣አርባምንጭ ከተማ፣ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ኢትዮጵያ መድህን ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ
ኦስካር በልብ ህመም ምክንያት ሆስፒታል መግባቱ ተሰማ