የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ማህበረሰቡን ከቱርካና ሐይቅና ከኦሞ ወንዝ ሙላት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በስፍራው በመገኘት ተመለከቱ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ማህበረሰቡን ከቱርካና ሐይቅና ከኦሞ ወንዝ ሙላት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በስፍራው በመገኘት ተመለከቱ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ማህበረሰቡን ከቱርካና ሐይቅና ከኦሞ ወንዝ ሙላት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የቱርካና ሐይቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑ እየጨመረና በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል ለዘርፈ ብዙ ችግሮች መዳረጉ ይታወቃል።

በመሆኑም የዞኑ አስተዳደር ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታት 7.2 ኪሎ ሜትር የዳይክ ስራና የውሃ ማፋሰሻ እንዲሰራ መደረጉ ተጠቁሟል።

ይሁን እንጂ ውሃው በአሁኑ ወቅት በፍጥነት ተጉዞ ከኦሞራቴ ከተማ 2 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ በከተማው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ደቅኗል።

በመሆኑም የክልሉ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ ከመስጠት አንጻር ከፌደራል አካላት ጋር በመመካከር በጥናት ላይ የተመሠረተ የዳይክ ስራና ውሃውን የማፋሰስ ስራ እንዲጀመር አድርጓል።

ኢንጂነር አክልሉ ስራው ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት የተጀማመሩ ስራዎች የሚበረታቱ እንደሆነ ገልጸው ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ያሉትን ችግሮች በመፍታት በፍጥነት መሠራት እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከክል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡