የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በየደረጃዉ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ አስታወቀ
የመስኖ ፕሮጀክቶችን በታቀደላቸዉ ጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ቢሮዉ ገልጿል፡፡
በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳና በአረካ ከተማ በሚሰራዉ የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በክልሉ መንግስት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ እንደሚሰራም አስታዉቋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤካል ነትር፤ በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳና በአረካ ከተማ በሚሰራዉ የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በተመለከተ በሰጡት መግለጫ በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር በ2021 በደቡብ ዉሃ ስራዎችና ክሮስላንድ በተባሉ በሁለት ኮንትራክተሮች ጋር ዉል ተገበቶ ስራዉ የተጀመረ ሲሆን በካሳ ክፍያ፣ ከዲዛይን ማሻሻያና ከኮንትራክተሮች ዝቅተኛ አፈፃፀም ጋር በተያይዘ ስራዉ መቋረጡን አንስተዋል፡፡
ክልሉ ከፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር የጋራ ዉይይት በማድረግ ተግባራትን በመከፋፈል በክልሉ የወላይታ ዞን አስተዳደር የወረዳና የከተማ አስተዳደሩን በማስተባበር 3 መቶ 81 የሚሆኑ የልማት ተነሺዎችን በመለየት ወደ 1 መቶ 10 ሚልየን ብር የካሳ ክፍያ ግምት መሰራቱን አብራርተዋል፡፡
ክልሉም በጀት ሲፀድቅ 60/40 በሚል የክልሉ አዋጅና ደንብ መሰረት ክፍያ ለመፈፀም ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ልማቱ ከሚከናወንበት አካባቢ ባለንብረቶቹ ከተነሱ በኋላ ወደ ስራ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
አክለዉም በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በክልሉ ርዕስ መስተዳድር ሆን ተብሎ ስራዉ እንዲቋረጥ የተደረገ አስመስሎ የሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎች ትክክለኛ እንዳልሆነና ይህ የወይቦ የመስኖ ፕሮጀክት ተጠናቆ የቦሎሶ ሶሬ ወረዳና የአረካ ከተማ ማህበረሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ክልሉ በአቋም እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን
የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በየደረጃዉ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ አስታወቀ

More Stories
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ማህበረሰቡን ከቱርካና ሐይቅና ከኦሞ ወንዝ ሙላት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በስፍራው በመገኘት ተመለከቱ
የህዳሴው ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ያሳኩት የጋራ ድል መሆኑን የጨታ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ
በዶሮ እርባታ ስራ በመሰማራታቸው የገቢ ምንጫቸውን ከማሳደግ ባሻገር ለሌሎችም የሥራ እድል መፍጠር መቻላቸውን በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ ማህበራት ገለጹ