በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ

ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር እና ከክልሉ የተውጣጣ ልዑክ በሀላባ ዞን ወይራ ዲጆ ሲምቢጣ ቀበሌ ጉብኝት እያደረገ ነው።

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የግብርና ሚንስትሩ ዋና አማካሪ አቶ ማርቆስ ሌረንጎ፤ ህብረተሰቡን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የተሰራው ስራ ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ማዕረጉ ማቲዎስ፤ በክልሉ በ35 ወረዳዎች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በተሰራው ስራ ከ318 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በጎርፍና በደራሽ ውሀ ምክንያት ተደጋጋሚ መፈናቀል ይደርስባቸው እንደነበር ገልፀው፤ የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ከምግብ ዋስትና ባለፈ የገቢ ምንጭ እንዳገኙ ተናግረዋል።

ፕሮግራሙ ጦሙን ያድር የነበረውን መሬት ከማልማት ባለፈ በዝናብ ወቅት ይፈጠር የነበረውን የጎርፍ አደጋ በመከላከል 350 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው ብለዋል።

የሲምቢጣ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም 41.5 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ ነው።

ዘጋቢ፡ ራሄል አሊ