ነጋዴው ማህበረሰብ በወቅታዊ ሁኔታዎች ሳይሸበር ኑሮን በማረጋጋት ለመንግስት ያለውን አጋርነት ሊያረጋግጥ እንደሚገባ በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
ወቅታዊ የንግድ ዋጋ ሁኔታና በከተማው ለሚከናወነው የኮሪደር ልማት የነጋዴውን ማህበረሰብ አስተዋጽኦ በማጠናከር የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ምክክር በሃና ከተማ ተካሂዷል።
የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኩሻቦ ኩሲያ እንደገለፁት፤ በወረዳው የንግድ ሥርዓቱን ለማሻሻል እንደ መንግሰት የቁጥጥርና የክትትል ሥርዓቱን በማጠናከር በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
ይሁን እንጅ አሁን ላይ በተለያዩ ወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት በነጋዴው ማህበረሰብ የሚስተዋሉ የሚዛን ማጭበርበር፣ ህገ-ወጥ የመንገድ ዳር ንግድና ግብይት፣ ከንግድ ፍቃድ ውጪ መነገድና ሌሎችም የሙስና አመለካከቶች እና ድርጊቶች ሊታረሙ እንደሚገባ አፅንኦት ስጥተዋል።
የሳላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ በበኩላቸው፤ ለውጥ ማምጣት የሚቻለው ልማትን በማረጋገጥ በመሆኑ ከሙስና የፀዳ ፍትሐዊ፣ አሳታፊ፣ ተአማኒ የሆነ ሥርዓት በመዘርጋት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
በመሆኑም ነጋዴው የማህበረሰቡ ልማቱ አንድ አካል እንደመሆኑ በወቅታዊ ሁኔታዎች ሳይሸበር ኑሮን በማረጋጋትና በሌሎችም ልማቶች ለመንግስት ያለውን አጋርነት በማረጋገጥ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
እንደ ወረዳ የቁጥጥርና ክትትል ሥርዓት ክፍተት፣ ህገ-ወጦችን አስተማሪ ቅጣት ከመቅጣት አንፃር ያሉ ክፍተቶችና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንደ መንግስት ትልቅ ትኩረት የሚሹ ስለመሆናቸው ተሳታፊዎች አንስተዋል።
የመድረኩ መሪዎችም እንደ ተቋም ከሰው ኃይልና ሌሎችም አንፃር ክፍተቶች ቢኖሩም ነጋዴው በተግባባው ልክ በጋራ በትብብር እና በቅንጅት መስራት ከቻለ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በማመን ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል።
አንዳንድ ጊዜ ከጂንካ-ሃና መንገድ ላይ በህጋዊ ነጋዴ ማህበረሰብ ላይ የሚስተዋሉ ያልተገቡ መጉላላቶች ተገቢ ባለመሆናቸው ተቋሙና የወረዳው አስተዳደር ከዞኑ የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እየሠራ መሆኑን ኃላፊዎቹ ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
በሩብ ዓመቱ 3.7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ገለጹ
የማር ምርት እጅግ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጎምቦራ ወረዳ በንብ ማነብ ስራ የተሠማሩ አርሶአደሮች ተናገሩ
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሰ የግብርና ልማት ላይ አደጋ እንዳያስከትል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ