የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት ስራ ማስፈፅሚያ 5 ቢሊዬን 108 ሚሊዬን ብር በላይ በጀት አፅደቀ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመትና የ2018 በጀት ዓመት ስራ ማስፈፅሚያ ከ5 ቢሊዬን ብር በላይ በጀት በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን የ2017 ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 ጠቋሚ ዕቅድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁ፥ በበጀት ዓመቱ በዋና ዋናና የሆልቲ ካልቸር ሰብሎች 187ሺ 247ሄ/ር መሬት በዘር መሸፈኑን ገልፀው፥ በዚህም 4 ነጥብ 1 ሚሊዬን ኩንታል ምርት እንደሚሰበሰብ አመላክተዋል።
ከቡና ምርትና ምርታማነትን አንፃር በበጀት ዓመቱ የታጠበና ያልታጠበ ቡና ጨምሮ 23ሺ 131ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉን ጠቁመው፥ በበጀት ዓመቱ 56 ሚሊዬን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 47 ነጥብ 2 ሚሊዬን ችግኞችን መትከል መቻሉን አቶ ሀብታሙ ካፍቲን ተናግረዋል።
በዞኑ ለኢንቨስትመንት የሚውል 1ሺ 282ሄ/ር መሬት በመለየት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለተሰማሩ የግል ባለሀብቶች በ145 ፕሮጀክቶች ድጋፍና ክትትል በማድረግ አፈፃፀሙ 70 ፕርሰንት መሆኑን አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል።
ከጤና ልማት አንፃር የወባ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንዲሁም የወባ በሽታ ምጣኔን ለመቀነስ በርካታ ስራዎች መሰራቱን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው አቶ ሀብታሙ፥ የኬሚካል ርጭት ያቆሩ ቦታዎችን የማፍሰስና የማዳፈን እንዲሁም ለ3 አመት የሚያገለግል 348ሺ 100 የአልጋ አጎበር ስርጭት መደረጉን ተናግረው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በተጨማሪ ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃማ ለማድረግ የጤና ፋርማሲ በሁሉም ወረዳዎች በማቋቋም የመድሀኒት እጥረት ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል ።
በበጀት ዓመቱ የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ ከ1ኛ -12ኛ ክፍል184ሺ 875ተማሪዎችን ለመቀበል ዓቅዶ 133ሺ 803 ተማሪዎችን ማሳካት የተቻለ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 8ሺ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል።
የትምህርት ቤት ገቢ አሰባሰብን በ2018 በጀት በማጠናከር የትምህርት ተደራሽነትንና እና ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
ከምክር ቤት አባላት የተነሱ የናፍጣና ቤንዚል እጥረት፣ የትራንስፓርት ታሪፍ ጭማሪ፣ የመሬት ወረራ፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ፥ ከመሬት ወረራ ጋር ተያይዞ ጉሩፈርዳ ወረዳ ላይ የተፈጠረውን ችግር ከክልል ጋር በመነጋገር በአፍጣኝ መፍትሔ ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል ።
ከናፍጣ እና ቤንዝል ጋር ተያይዞ ገለልተኛ አካል በማደራጀት ቁጥጥር ስራ ከመስራት ባለፈ እጥረት ለመፍጠር በሚጥሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።
ምርጥ ዘር ግብዓት ላይ ያለው የአመለካከት ችግር ለበርካት አመታት ማነቆ እንደነበር የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው፥ አሁን ላይ አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግና ተጠቃሚነቱን እያረጋገጡ የመጡበት ሂደት መኖሩን ጠቁመው፥ በጉራፈርዳ እና ሸይ ቤንች ምርጥ ዘር ላይ የተፈጠረው ችግር የምርጥ ዘር አቅራቢ ድርጅት እንዲተካ የተደረጉበት ሂደት መኖሩን ገልፆ በቀጣይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን ለምክር ቤቱ አስፈፃሚ አካላትና የፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትቶችን ሾመት ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን፥ አቶ ሄኖክ አባጅፍር – የቤንች ሸኮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ በየነ ብርሃኑ – ፕላን እና ልማት መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ ግሩም ተማም – የውሀ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ፣ ወልደየስ ዘለቀ – የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ስፓርት መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ ማቲዎስ ከይሳ – ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምራያ ኃላፊ፣ አቶ መሰረት ሞገስ – የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ ወንድሙ መንገሻ – የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት፣ አቶ ሰለሞን ፃኑ – የሲዝ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት እንዲሆኑ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል ።
ምክር ቤቱ የቀረቡትን ሹመቶች በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ በማፅደቅ ተሿሚዎች ቃለመሃላ ፈፅመዋል ።
በመጨረሻም የቤንች ሸኮ ዞን የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ብርሃኔ በዛብህ የ2018 በጀት 5 ቢሊየን 108 ሚሊየን 447 ሺህ 200 ብር ከ69 ሳንቲም ሆኖ እንዲጸድቅ ቀርቦ የምክር ቤቱ አባላት የቀረበውን ረቂቅ በጀት ተቀብሎ በማፅደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ዮናስ ወ/ገብርኤል – ከሚዛን ጣቢያችን
የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት ስራ ማስፈፅሚያ 5 ቢሊዬን 108 ሚሊዬን ብር በላይ በጀት አፅደቀ

More Stories
በመኸር እርሻ ከሚለሙ ስብሎች ጥሩ ምርት ለማግኘት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ እንደሚገኙ በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሣ ወረዳ የሚገኙ አርሶአደሮች ተናገሩ
ነጋዴው ማህበረሰብ በወቅታዊ ሁኔታዎች ሳይሸበር ኑሮን በማረጋጋት ለመንግስት ያለውን አጋርነት ሊያረጋግጥ እንደሚገባ በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
በ2016 እና በ2017 ዓ.ም ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ የግብርና ግብዓቶችን በማቅረብ አደይ መንግስታዊ ፕሮግራም በአሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ሥራ አጥ ወጣቶችን ወደ ሥራ እያስገባ መሆኑን አስታወቀ