በአንዱዓለም ሰለሞን
የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች ቀን በቅርቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ ውሏል፡፡ በዚህ መነሻ፣ ለዛሬ ስለአንድ አንጋፋ የሀገራችን የስፖርት ጋዜጠኛ ጥቂት እላችሁ ዘንድ ብእሬን አነሳሁ፡፡
ምንም እንኳ ዛሬ በህይወት ባይኖርም፣ በኢትዮጵያ ራዲዮ የስፖርት ፕሮግራም ዝግጅት ክፍል ከቀደምቶቹ ጋዜጠኞች ስሙ በዋንኛነት ይጠቀሳል፡፡ በእርግጥም እርሱ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ላይ ታላቅ ተጽዕኖን ያሳደረ ስመ ጥር ባለሙያ ነበር፤ ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ፡፡
ለአራት አስርት ዓመታት በሙያው ሀገሩን ያገለገለውና በሰራቸው ስራዎች በአያሌ ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ የቀረው ደምሴ፣ በዘገባዎቹና በቀጥታ ስርጭት ባስተላለፋቸው የስፖርት ውድድሮች ዛሬም ድረስ በብዙ የስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ የሚታወስ ነው፡፡
እዚህ ላይ ለአብነት በ1980 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደውን የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታ ላንሳ። ጨዋታው ኢትዮጵያን ከዚምባቡዌ አገናኝቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1ለ0 እየተመራ መደበኛው 90 ደቂቃ ሊያበቃ ተቃርቦም ነበር፡፡
በዚህ አስጨናቂ ሰዓት ግን፣ የስታዲየሙን ተመልካች በደስታ ጮቤ ያስረገጠ ክስተት ተከሰተ፡፡ ይህ ክስተት የደጋፊውን ብቻ ሳይሆን በወቅቱ ጨዋታውን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ያስተላልፍ የነበረውን ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤን ጭምር ያስደሰተና እጅግ ስሜታዊ ያደረገ ነበር፡፡-
“አማኑኤል ለሙሉዓለም፣ ሙሉዓለም፣ ለመንግስቱ ሁሴን፣ መንግስቱ ሁሴን ለአማኑኤል፣ ሙሉ ዓለም፣ ሙሉዓለም አሻማ፣ ወይኔ ገብሬ፣ ገብሬ የመታውን፣ የዚምባቡዌ 2 ቁጥር በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳረፈ!”
ደምሴ ዳምጤ በታላቅ ሲቃ ውስጥ ሆኖ በስታዲየም ላልተገኘው፣ በተለይም ደግሞ ጨዋታውን በራዲዮ በመከታተል ላይ ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ መልኩ ነበር ክስተቱን የገለጸው፡፡ በጎሏ መቆጠር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተስፋ ለመለመ፡፡ የስታዲየሙ ድባብም ተቀየረ፡፡
መደበኛው የ90 ደቂቃ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት ተጠናቆ፣ ጨዋታው ወደተጨማሪ 30 ደቂቃዎች አመራ፡፡ ያም ሆኖ፣ ሁለቱ ቡድኖች ምንም ጎል ባለማስቆጠራቸው ወደመለያ ምት አመሩ፡፡
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወገን፣ ከአምስቱ የፍጹም ቅጣት ምቶች ሁለቱ መከኑ፤ በቀለ የመታት ኳስ ወደውጪ ስትወጣ፣ የመንግስቱን ግብ ጠባቂው አዳነበት፡፡ የዚምባቡዌ ተጫዋቾች ከመቷቸው የፍጹም ቅጣት ምቶች ውስጥ ደግሞ ግብ ጠባቂው ተካበ ዘውዴ ሁለቱን አዳነ፡፡
በዚህ መሰረት ውጤቱ 3ለ3 ሆነ፡፡ ቀጣዩ ከሁለቱም ወገን አንድ አንድ የፍጹም ቅጣት ምት እየመቱ የሚቀጥሉበት ነው፡፡ አንዱ ስቶ ሌላኛው ካገባ ጨዋታው ጎል ባስቆጠረው ቡድን አሸናፊነት ይጠናቀቃል፡፡
የዙምባቡዌው 3 ቁጥር የፍጹም ቅጣት ምቱን ለመምታት ተዘጋጀ፡፡ ተካበም ግቡን ለመጠበቅ ቦታውን ያዘ፡፡ በዚህች የጭንቅ ሰዓት፣ ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ኳሷ ከመመታቷ አስቀድሞ አንድ ቃል ከአንደበቱ ወጣ፤ “ውጪ፣ ውጪ” የሚል ቃል፡፡ በጭንቅ ያፈተለከ፣ ግን ደግሞ እንደ ትንቢት አልያም እንደንግርት ወይም እንደቅድመ ግምት ያለ ነገር ነበር፡፡
ነገሩ ደምሴ አስቀድሞ እንደተመኘው ብሎም በአንደበቱ ጭምር እንዳወጣው ሆነ፤ የዚምባቡዌው ተጫዋች የመታት ኳስ ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ደምሴም በዚያው ቀጥሎና በታላቅ ስሜት ውስጥ ሆኖ፡-
“ውጪ፣ ውጪ ሰደዳት!” ሲል በደስታ ሳቅ አጅቦ ሁኔታውን ለተጨነቀው የራዲዮ አድማጭ ገለጸ፡፡ ዝነኛው ጋዜጠኛ በአንድ ወቅት ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃለ መጠይቅ፣ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ በማለት አስተያየቱን ሰጥቶ ነበር፡-
“የዚምባቡዌው ተጫዋች ገና ኳሷን ሳይመታ ውጪ ውጪ እላለሁ፡፡ ለሚሰማው ሰው ኳሱ ተመቶ ውጪ የወጣ ይመስላል፤ ግን አልተመታም። ውጪ፣ ውጪ ስል፣ ውጪ ለቀቃት፡፡ እኔም ‹ውጪ ሰደዳት› ብዬ በሳቅ ጨረስኩት፡፡”
ወደጨዋታው ልመልሳችሁ፡፡ ክስተቱ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ አጋጣሚን ፈጠረለት፡፡ የስታዲየሙ ተመልካች በደስታ፣ በጉጉትና በተስፋ ስሜት ተወጠረ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህችን ዳኛቸው ኳሷን እስኪመታ ድረስ ያለችውን አስጨናቂ ቅጽበት፣ በታላቅ ጸጥታ ውስጥ ሆኖ ጠበቃት፡፡ ደምሴ ደግሞ ሁኔታውን እንዲህ ገለጸው፡-
“አሁን ዳኙ ሊመታ ነው… ወይኔ ዳኙ፣ ጨፈረ ደነሰበት፡፡ ደንሶ አገባ ዳኙ! በጣም አስደናቂ ግብ ነው! አታለለው፣ ቀኙን አሳይቶ ግራውን፣ ግራውን አሳይቶ በቀኙ!…”
በወቅቱ የሀገራችን ፕሬዚዳንት የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ሀ/ማርያም ሳይቀር በስታዲየም ተገኝተው በተከታተሉት በዚህ የፍጻሜ ጨዋታ፣ ኢትዮጵያ አሸነፈች፡፡ በመላ ሀገራችን ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡ የስታዲየሙ ድባብ ፍጹም ልዩ ነበር፡፡ ተመልካቾቹ “እንደተመኘኋት አገኘኋት” እያሉ በአንድነት ጨፈሩ፡፡
ደምሴ በደስታ ሰከረ፡፡ በአንድ ወቅት ጨዋታውን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃለ ምልልስ እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር፡-
“ይህ ጨዋታ ድል ያገኘንበት፣ በጣም የተደሰትኩበት፣ ህሊናዬን የሳትኩበት፣ ስሜታዊነቴም ጎልቶ የወጣበት ነው፡፡”
በስፖርት ማሸነፍ እንዳለ ሁሉ መሸነፍም ያጋጥማል፡፡ በዚህ ረገድ፣ በተለይም በእግር ኳሱ ደምሴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታላቅ የውድድር መድረክ ድል ሲቀዳጅ ለማየት ሳይታደል ነው ያለፈው፡፡ ቡድኑ በገጠመው መራር ሽንፈት ከብስጭት አልፎ የታመመባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ብሔራዊ ቡድኑ በአንድ ወቅት በግብጽ 6ለ0 የተረታበት ጨዋታ ይጠቀሳል፡፡ ይህን አስመልክቶም፡-
“እግር ኳስ ህመምተኛ ቢያደርገኝም፣ ቂም አልያዝኩበትም፡፡ ብዙ ወጣት አምሳያዎቼን እንደተካሁ ይሰማኛል” በማለት ተናግሮ ነበር፡፡
ወደሌላ ታሪክ ልውሰዳችሁ፤ እ.ኤ.አ 1992፣ በስፔን የባርሴሎና ኦሎምፒክ ዓለም አንድ አስደናቂ ክስተት ተመለከተ፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ በታላቁ የውድድር መድረክ ያሸነፈች መጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት አትሌት ያሰኛትን ድል በ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ተቀዳጀች፡፡
ጠይሟ እንቁ በባርሴሎና ሰማይ ስር በአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለማት ደምቃ ስትታይ፣ ሰንደቅ ዓላማችን በክብር ከፍ ብሎ ሲውለበለብ፣ ብሔራዊ መዝሙራችን ሲዘመር፣ ዓለም በክስተቱ ሲደመም፣ በቀጥታ ስርጭት ውድድሩን በቴሌቭዥን ሲያስተላልፍ የነበረው ጋዜጠኛ “…the first ever gold medal for Ethiopia!” እያለ ሲዘግብ፤ በርካታ ኢትዮጵያውያን ግን ይህን ለማየትም ሆነ ዜናውን ለመስማት አልቻሉም፡፡
በወቅቱ እንዲህ እንደዛሬው መረጃ በቀላሉ ለማግኘት አይቻልም፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያው አንድ ነበር፡፡ እሱም ቢሆን የሚሰራው የተወሰነ ሰዓት ነው፡፡ ብቸኛው የራዲዮ ጣቢያ ደግሞ ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ የሚገኘው ነበር፤ የኢትዮጵያ ራዲዮ። ውድድሩ ደግሞ በእኩለ ሌሊት ነበር የተደረገው።
ደምሴ ይህን የድል ዜና ሲሰማ ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡ በእርግጥም ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው አፍሪካ ኩራት የሆነው ይህ የድል ዜና እንቅልፍ የሚነሳ ነበር፡፡ ሀገር ወዳዱ ጋዜጠኛ እረፍት አጣ፡፡ እናም በዚያ ሌሊት ወደ ራዲዮ ጣቢያው ለመሔድ ወሰነ፡፡
ዘገባውን ሲያጠናቅር አድሮ፣ በጠዋት የድል ብስራቱን ዜና ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊያደርስ ሳያመነታ ተነሳ፡፡ በዚያ ሌሊት አራት ኪሎ ቀበና ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ፣ አቡነ ጴጥሮስ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ራዲዮ አመራ፡፡
የሚስቱን ተማጽኖና “አንተ ሰው ጅብ እንዳይበላህ!” የሚል ማስፈራሪያ ቸል ብሎ፣ በሀገር ፍቅር ስሜት በውድቅት ሌሊት በእግሩ ተጓዘ፡፡ እንዳሰበውም በጠዋት ዜናውን ለኢትዮጵያዊያን አደረሰ፤ “እንኳን ደስ አላችሁ!” በማለት፡፡
ደምሴ ማለት ይህ ነው፤ ሀገሩን የሚወድና ሙያውን የሚያከብር፥ ለብዙዎች ዓርዓያ የሆነ ድንቅ ጋዜጠኛ!
በ1947 ዓ/ም የተወለደው ደምሴ ዳምጤ፣ ለስፖርት ፍቅር ያደረበት ገና በታዳጊነቱ ተማሪ ሳለ ነበር፡፡ በእረፍት ሰዓት ለተማሪዎች ስለስፖርት ያወራላቸው ነበር፡፡ ይህን የታዘቡት አንድ መምህሩ በሚኒ ሚዲያ የስፖርት ዘገባ እንዲሰራ አደረጉ፡፡
ከዚህ በሻገር፤ ድሬዳዋ ሲሚንቶ ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩት አባቱ አስተዋጽኦም ሌላው እዚህ ላይ የሚጠቀስ ነው፡፡ ጨዋታ ሲኖር ከአባቱ ጋር ወደስታዲየም ይሔድ ነበር፡፡ ጨዋታ ከማየት ባሻገር፣ ዘገባ መስራት የጀመረውም በዚያ አጋጣሚ ነበር፤ ገና በ13 ዓመቱ፡፡
እዚህ ላይ ደራሲ አፈንዲ ሙቀቲ በአንድ መጽሀፉ ስለተወዳጁ ጋዜጠኛ ያስነበበውን ልጥቀስ፡-
ደምሴ የስፖርት ጋዜጠኝነቱን የጀመረው በድሬዳዋ ይካሄዱ የነበሩትን ውድድሮች በአማተርነት በመዘገብ ነበር። ሪፖርቱን በፖስታና በስልክ እያደረገ ለእውቁ ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ ያስተላልፋል። ሰለሞንም “ወጣት ደምሴ ዳምጤ ከድሬዳዋ እንደዘገበው” በማለት በራድዮ ያቀርበዋል። አራት አመት ሙሉ እንዲህ ሲያደርግ፣ ሰለሞን ደምሴን በአካል አያውቀውም።
ታድያ በአንድ ወቅት ትልቅ የስፖርት በአል በድሬ ዳዋ ሊከበር ፕሮግራም ተያዘ። ሰለሞን ተሰማም ለበአሉ ተጋብዞ በአውሮፕላን ድሬዳዋ ሄደ። ደምሴ ሰለሞንን ከአየር ማረፊያ ተቀብሎ ወደ ድሬዳዋ ስፖርት ጽ/ቤት እንዲያመጣው ታዘዘ።
ደምሴም እንደታዘዘው ከአየር ማረፊያው ሄዶ ሰለሞንን ተቀበለው። ሻንጣውን ይዞ መኪና ላይ ጫነለት። ሰለሞንም ‘’ጎሽ የኔ ልጅ” ብሎ ከኪሱ አንድ ብር አውጥቶ ሰጠው። ከዚያም በቀረበለት መኪና ወደ ድሬዳዋ ስፖርት ጽ/ቤት ሄደ። ደምሴም ቀስ እያለ በታክሲ ተከተለውና ከጽ/ቤቱ ደረሰ።
ሰለሞን ደምሴን እንዳየው፡-
‘’ጩሎ! ቅድም አንድ ብር ሰጥቼሽ የለ እንዴ? አሁን ደሞ ለምን መጣህ” በማለት ጠየቀው። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች፡-
‘’እንዴ! ይሄ እኮ ወጣት ደምሴ ዳምጤ ከድሬዳዋ እንደዘገበው እያልክ ስሙን የምትጠራለት ያንተው ሪፖርተር ነው” አሉት። ሰለሞን በስህተት የደምሴን ስሜት የጎዳ መስሎት ደነገጠ። ቶሎ ብሎም ከአንዱ መደብር በመግባት ሙሉ ልብስ ገዛለት።
የደምሴን አንድ ሌላ አስቂኝ ገጠመኝ ደግሞ ላክልላችሁ፡፡ ይህንንም ያገኘሁት ከዚሁ መጽሀፍ ላይ ነው፡-
ደምሴ ዳምጤ በድሬዳዋ ያሳለፈው ሌላ አስቂኝ ትዝታም አለው። አቶ ስለሺ ማንደፍሮ የሚባሉ ሰውዬ በዳኝነት ተመድበው ድሬዳዋ ይሄዳሉ። የኤርትራው እምባሶይራ ቡድን ከአንድ የድሬዳዋ ቡድን ጋር የሚጫወተውን ጨዋታ መምራት ይጀምራሉ። ደምሴም ለእሱ በተወሰነች ጥግ ላይ ሆኖ የጨዋታውን ውሎ መመዝገብ ይጀምራል።
ከአፍታ በኋላ ግን በተጫዋቾቹ መካከል ረብሻ ተነሳ። ዳኛው ጨዋታው እንዲቋረጥ አደረጉ። ከዚያም በሽቦ በታጠረው ጥብቅ ክልል ውስጥ ያለውን ሰው ሁሉ ማስወጣት ጀመሩ። ደምሴ ካለበት ቦታም በመሄድ ‘’ውጣ!’’ አሉት። ‘’እንዴ እኔ እኮ አማተር ጋዜጠኛ ነኝ” ቢላቸው ሊሰሙት ነው? ’’ውጣ ነው የምልህ ውጣ’ ’በማለት አባረሩት።
ደምሴ በዳኛው ድርጊት ተናደደ። እናም ዘገባውን ሲጽፍ ‘’ዳኛው ከመናደዳቸው ብዛት ፊሽካውን መያዝ አቅቷቸው በቂጡ ሲነፉት ነው የዋሉት የሚል ሃረግ አከለበት። ይህ ከተፈጠረ ከአራት አመታት በኋላ፣ ደምሴ የኢትዮጵያ ሬድዮ ጋዜጠኛ ሆኖ ተቀጠረ።
የስፖርት ዘገባ እንዲሰራም ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም ተላከ። ነገር ግን፤ መጥፎ እጣ ገጠመው። ገና ከዋናው የስታድየም በር ገባ እንዳለ ከዚያ “ንዴተኛ ዳኛ” ጋር ፊት ለፊት ተገጣጠመ። ደምሴ ለጊዜው ደንገጥ ቢልም ዳኛው ነገሩን ረስተውት ይሆናል በሚል ተስፋ ራሱን በማጽናናት ወደ ፊት ለመግፋት ሞከረ።
ግና ሰውዬው የዋዛ አልነበሩም። “አንተ! የድሬዳዋ አሸዋ በአናትህ ይነፋና እኔ ነኝ ፊሽካ በቂጡ የምነፋው?’’ በማለት እየተንደረደሩ ወደ እሱ መጡ። ደምሴ ተብረከረከ። ትንፋሹን ሰብሰብ አድርጎ ፈትለክ አለ።
ከዚያ የሮጠ መሿለኪያ ሃዲዱን እስኪሻገር ድረስ ዞር አላለም። በኋላ ግን ሰው እንዳልተከተለው ጠረጠረ። እናም ዘወር ብሎ ሲያይ ዳኛው ከኋላው የሉም። በዚያም ‘’አይ ሞኝነቴ’’ እያለ ለብዙ ጊዚያት ሲስቅ ከርሟል።
ጥቅምት 26 ቀን 2005 ዓ/ም ኢትዮጵያዊያን መጥፎ ዜና የሰሙበት ቀን ነበር፤ ያ በሰበር ዜና የስፖርተኞቻችንን ድል ሲያበስረን የነበረው ድምጸ መረዋው ጋዜጠኛ ህልፈቱ የተሰማበት፡፡ የደምሴ ሞት፣ ብዙዎችን ያሳዘነና ያስደነገጠ ነበር፡፡
ከብዙዎቹ አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ ኤፍሬም የማነ፣ ክስተቱንና ቀኑን እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው፡-
“የኢትዮጵያ የስፖርት ሚዲያ ፍራሽ አውርዶ መሬት የተቀመጠበት ቀን!”
“እግር ኳስ ቢያሳምመኝም ቂም አልያዝኩበትም”

More Stories
“በእጅ ጋሪ ያመላልሱኝ ነበር” – ተወዳ መንጌ
የስም ነገር
“ስነጽሁፍ ላይ ያለኝን እውቀት ያመጣሁት በተመስጦ በማድመጥ ነው” – ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበቡ በለጠ