ዘርፉን ለማጠናከር የሚያስችል የባለድርሻ አካላት ውይይት መድረክና የግብርና ግብዓት ኤግዚቪሽን በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።
የግብርና ምርቶችን ማስተዋወቅ ለዘርፉ እድገት ያለው አበርክቶ ከፍተኛ በመሆኑ ኤግዚቪሽን መዘጋጀቱ ተመላክቷል።
በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በቢሮው የሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ፤ የማህበረሰቡን የአመራረትና የአመጋገብ ሥርዓት ጤናማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በሀገር ደረጃም ሆነ በክልሉ በርካታ የከርሰ-ምድርና የገጸ-ምድር ጸጋዎችን በአግባቡ በማልማትና በመጠቀም ማህበረሰቡን ከምግብ እህል እጥረት ችግር ማውጣት ይገባል ነው ያሉት።
ክልሉ አጠቃላይ 3 ነጥብ 91 ሚሊየን ሄክታር የቆዳ ስፋት፣ ከ4 ነጥብ 19 ሚሊየን በላይ የህዝብ ቁጥር፣ 23 በመቶ ያህል የደን ሽፋንና አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች መኖራቸው ለዘርፉ መልካም አጋጣም መሆናቸው በውይይት ሰነዱ ተመላክቷል።
በፍራፍሬ ምርቶች ከ163 ሺህ 1 መቶ በላይ ማሳ በማልማት ከ19 ሚሊየን 921 ሺህ በላይ ኩንታል ምርት ማግኘት የተቻለ ሲሆን በሥራሥር ምርቶች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
በኤግዚቪሽኑ ምርትና አገልግሎታቸውን ካቀረቡ ድርጅቶች መካከል የድንች ዘር አባዥ አቶ አየለ ወልደጊዮርጊስና ረንግቬት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግብርና ኬሚካል አቅራቢ ድርጅት አስተባባሪ አቶ ፋንታሁን ንጉሴ፤ የተሻሻሉ ግብዓቶችን በማቅረብ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሆነ ተናግረዋል።
ምርቶቻቸው የጥራት ደረጃቸውን ያሟሉ ስለመሆናቸው ገልጸው በቀጣይ በክልሉ የሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ያሉ የዘር፣ ኬሚካል አቅርቦትና የጥራት ችግሮች ላይ በቅንጅት ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በግብርና ግብዓቶች ኤግዚቪሽን ጉብኘትና ምክክር ተደርጎ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ አሳምነው አትርሳው – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
በስብዕና ግንባታ ስራ ላይ በማተኮር በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ገለፀ
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለአረጋዉያን ያስገነባዉን የመኖሪያ እና እንክብካቤ ማዕከል ስራ አስጀመረ
የትምህርት ዘርፍ መጠናከር ሀገሪቱ ወደ አዲስ የስልጣኔ ማማ ለመድረስ ለምታደርገው ጉዞ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ