ሀዋሳ፡ ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በተገቢ መደገፍና ማበረታታት ለሃገር ኢክኖሚ እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በ2 ነጥብ 6 ሚልዮን ብር ለሚያስገነባው የማሳያና የመሸጫ ሼድ ግንባታ ህነፃ ስራ ጨረታ ካሸነፈው ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ርክክብ አድርጓል።
የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ምክትልና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ዙልፋ አለዊ በዚህ ወቅት እንዳሉት በ2007 ዓ/ም በቀድሞው ደቡብ ክልል በጀት አመት ተጀምረው የተቋረጡ የምርት መሸጫና ማሳያ ሼዶች እንደነበሩ አስታውሰው ይህ የወልቂጤ ሳይትም ከነዚያ መካከል አንዱ እንደነበር ጠቁመዋል።
በዚህም አሁን ላይ ክልሉ ስራውን በማስቀጠል በ2017 በጀት አመት አራት ሳይቶች ላይ የግንባታ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት ሃላፊዋ የወልቂጤ ሳይትም በ2018 በጀት አመት በመጀመሪያዎቹ ወራት ለማጠናቀቅ ታስቦ ጨረታውን ካሸነፈው አካል ጋር የውል ስምምነት ተጠናቆ በዛሬ እለት የሳይት ርክክብ መደረጉን ገልፀዋል።
በከተማው ለሚገኙ አምራች ኢንተርፕራይዞች በተገቢው ተጠቃሚ ለማድረግ ግንባታው የሚያከናውነው አካል በተያዘለት ጊዜ መስራት በጥራት እና በፍጥነት አጠናቆ ማስረከብ ይጠበቅበታልም ብለዋል።
የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በተገቢ መደገፍና ማበረታታት ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ይህ ግንባታ ሲጠናቀቅ በኢንተርፕራይዞች የተመረቱ ምርቶች በስፋት የሚታዩበትና የሚተዋወቁበት ተጨማሪ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ነው ያሉት።
እንደሃገር ዘላቂ እድገትና ኢኮኖሚው ወደላቀ ደረጃ እንዲመጣ የማኑፋክቸሪንጉን ዘርፍ ማሳደግ ይገባል ያሉት ወ/ሮ ዙልፋ ምርቶች እንዲተዋወቁና ይበልጥ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ቢሮው ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑንም አመላክተዋል።
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ የመተካት ስራ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ሃላፊዋ ለዚህ ማሳያ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቢሮዎች ሲደራጁ አብዛኛው የቢሮ ግብይት የተሟላ በሃገር ውስጥ ምርቶች እንደሆነም ጠቅሰዋል።
የሚገነቡ ሼዶች የግንባታ ጥራታቸውን በጠበቀና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁም የክልሉ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ክትትል እያደረገ እንዳለ ተናግረው፥ ስራውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በሚሰራው ስራ ሁሉም አካል ድጋፍና ክትትል ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
በሳይት ርክክቡ ወቅት የተገኙት በማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ባለሙያ አርክቴክት አቶ ሄኖክ ኑኔ እንዳሉት ከዚያ ቀደም ሊገነባ ተጀምሮ የተቋረጠውን የግንባታ ስራ ወደ ባለአንድ ፎቅ ደረጃ ለማሳደግ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ሄኖክ በማከልም ኮንትራክተሩ ጨረታውን ያሸነፈው ያለው ልምድና የባለሙያ ስብጥሩ ከግምት በማስገባት መሆኑና ባለስልጣኑ ከሚያደርገው ጥቅል የስራው ሁኔታ ከመከታተል ባሻገር የባልስልጣኑ ተወካይ መሃንዲስ በስፍራው በመገኘት በየቀኑ የግንባታ ጥራት ደረጃውን በመከታተል ስራውን የሚመራ ይሆናል ብለዋል።
በመሆኑም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የግንባታ ጥራቱን በጠቀ መልኩ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም ተናግረዋል።
ጨረታውን ያሸነፈው የአብ ቃል ኮንስትራክሽን ማህበር ሊቀመንበር አቶ አዳነ ገብሩ በበኩላቸው በ2 ሚልዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር ተወዳድረው ጨረታው ማሸነፋቸውን ገልፀዋል።
ማህበሩ ጨረታውን ካሸነፈበት ጊዜ ጀምሮ ለስራው የሚሆን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ መቆየቱን ያነሱት የማህበሩ ሊቀመንበር ለርክክብ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀድሞ ግንባታው በማጠናቀቅ ለማስረከብ እንደሚሰሩም አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ሚፍታ ጀማል – ከወልቂጤ ጣቢያችን
የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በተገቢ መደገፍና ማበረታታት ለሃገር ኢክኖሚ እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተገለጸ

More Stories
በጎፋ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 1 ሺህ 830 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡ ተገለጸ
በመኸር እርሻ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ይጠበቃል – የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ
በጌዴኦ ዞን የጎብኚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ ተገለጸ