ገቢ ከራስ ለራስ የሚዉል በመሆኑ በቴክኖሎጂ በተደገፈ የአከፋፈል ስርዓት በአጭር ቀናት ከታቀደው በላይ ግብር መሰብሰብ እንደሚገባ ተገለጸ

ገቢ ከራስ ለራስ የሚዉል በመሆኑ በቴክኖሎጂ በተደገፈ የአከፋፈል ስርዓት በአጭር ቀናት ከታቀደው በላይ ግብር መሰብሰብ እንደሚገባ ተገለጸ

ገቢ ከራስ ለራስ የሚዉል በመሆኑ የአከባቢ ልማትን ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ በተደገፈ የአከፋፈል ስረዓት በአጭር ቀናት ከታቀደዉ በላይ ግብር መሰብሰብ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ ፡፡

በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ/ም የግብር ዘመን የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የግብር ክፍያ ማስጀመርያ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉ ዋቆ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉ ዋቆ ግብር ከራስ ለራስ የሚዉል በመሆኑ የአከባቢልማትን ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ በተደገፈ የአከፋፈል ስረዓት በአጭር ቀናት ከታቀደዉ በላይ ገቢ መሰብሰብ እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡

አክለዉም በክልሉ በ3ት ደረጃዎች 125 ግብር ከፋዮች እንዳሉ ገልፀዉ ከእንዚህ 112ቱ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች መኖራቸዉን ጠቁመው፥ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ገቢ ለመሰብሰብ ተቀናጅቶ በመስራት ዉጤት በአጭር ጊዜ ማምጣት እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ጋልሺ፥ ግብር ለሀገር ኢኮኖሚ ዋናዉ የጀርባ አጥንት በመሆኑ የግብር አሰባሰብ ስርአቱን በአግባቡና በተቀናጀ መልኩ መምራት ሀገርን ከድህነት ለማላቀቅ ስለሚረዳ በዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል ፡፡

የጂንካ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማንጎ ከበደ እንደገለፁት በከተማዉ ካሉ 5ሺ ሁለት የደረጃ ግብር ከፋዮች 4 ሺ 622 የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ሲሆኑ በዚህ ሐምሌ ወር ዉስጥ በተቀመጡ 10 ቀናት ወደ 35 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅደዉ እየሰሩ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

በአስጎብኚና የልብስ ስፌት ዘርፍ ከተሰማሩ ግብር ካፋዮች መካከል አቶ ወንድማገኝ ላቀዉና አቶ ቢንያም ቸርሊሆን በጋራ እንደገለፁት በግብር መልክ የሚከፈለዉ ገቢ ተመልሶ ለራስ ጥቅም የሚዉል በመሆኑ ቀድመዉ ግብራቸዉን በመክፈላቸዉ ደስተኞች እንደሆኑና ሌሎችም ግብር ከፋዮች የመንግስትን ግብር በወቅቱና በታማኝነት መክፈል እንዳለባቸዉ ተናግረዋል ፡፡
በማስጀመርያ መርሃ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊን ጨምሮ የአሪ ዞን ገቢዎች መምርያ ኃላፊ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች የዞንና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች የንግዱ ማህበረሰብ እና የሀይማኖት አባቶች የተሳተፉ ሲሆን ግንባር ቀደም ለሆኑ ግብር ከፋዮችም የእዉቅና ሽልማት ተበርክቷል ፡፡

ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን