ዜጎች የራሳቸውን ጤና ማምረት እንዲችሉ የጤና ማጎልበትና የበሽታ መከላከል ሥራ ላይ የሚዲያ ተግባር ላቅ ያለ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዜጎች የራሳቸውን ጤና ማምረት እንዲችሉ፣ የጤና ማጎልበትና የበሽታ መከላከል ሥራ ላይ የሚዲያ ተግባር ላቅ ያለ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም አስታወቁ፡፡
በክልሉ ታርጫ ከተማ ከክልሉ በየደረጃው ለሚገኙ ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች በጤና ተግባቦት ዓላማ ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለጹት፤ በየደረጃው የሚገኙ ሚዲያዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች ለኅብረተሰቡ ተጨባጭ መረጃ መስጠት እንዲችሉ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና ነው።
የሚዲያው ዘርፍ ባለፉት ጊዜያት አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ረገድም የድርሻቸውን እየተወጡ መቆየታቸውንም በማስታወስ።
በክልሉ በጤና መከላከልና ማጎልበት ዘርፍ የዘመቻ ሥራ ሲኖር ተግባቦቱ እንዲኖር ለማስቻል በክልሉ በሚገኙ የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ቅርንጫፍ ጣቢያዎች በ12 ቋንቋዎች ትርጉም ያላቸው መልዕክቶች እንዲተላለፉ እየተሠራ እንዳለም ገልጸዋል።
በማናቸውም የጤና ልማት ዘርፍ የሚተላለፈውን የመልዕክት ይዘት በመረዳት በተዛቡ አስተሳሰቦች ሳቢያ በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚፈጠረውን መረበሽ ለማስቀረት መረጃ በማሰባሰብና በመተንተን ግልጽኝነትን ለመፍጠር አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ በመሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
የወረርሽኝ ቁጥጥርና ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ላይ እና የጤና አጀንዳዎችን ከማሣካት ረገድ የታዩ ክፍተቶች ለማረም፣ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል እንዲቻል ከሥልጠናው የተሻለ ግብኣት ይገኛል ተብሎ እንደሚታሰብም ገልጸዋል።
የሥልጠናው ሰነድ ቀርቦ ውይይት በሰፊው እንደሚደረግም ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዙሪያ የሚደረገው ጥንቃቄ በመቀዛቀዙ አሁንም የቫይረሱ ስርጭት እየተስተዋለ መሆኑን ተገለጸ
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የጤናው ዘርፍ ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አደረገ
እድሚያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የአንጀት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቆመ