በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል
ከቀኑ 7:00 በተጀመረው የመጀመሪያ እግር ኳስ ጨዋታ የደቡብ ኦሞ ዞን ተወካዩ ኛንግላድ ክለብ ከጋሞ ዞኑ ዳራማሎ ደንዳሾ የተጫወቱ ሲሆን ዳራማሎ 1ለ0 በመርታት ለፍፃሜው አልፏል።
በሌላ ጨዋታ ከቀኑ 9:00 በተደረገው ሁለተኛ ጨዋታ የባስኬቶ ዞን ተወካዩ ባስኬት ቡና እግር ኳስ ክለብ ከኮንሶ ዞኑ አቻው ኮንሶ ንዮርክ ጋር ተገናኝተው በመደበኛው 90 ደቂቃ 2ለ2 አቻ ወጥተው በመለያ ምት ባስኬት ቡና 3ለ1አሸንፎ ለፍፃሜ ጨዋታ ተሻግሯል።
በዚህም የፍፃሜ ወይም የዋንጫ ጨዋታ እሁድ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም በዳራማሎ ዴንዳሾ እና በባስኬት ቡና መካከል ከቀኑ 8:00 የሚደረግ ሲሆን ከዚያ ቀደም ብሎ በ6:00 ኛንግላድ ከኮንሶ ንዮርክ 3ኛ ደረጃ ለመውጣት በጂንካ ሁለገብ ስታዲዬም ይጫወታሉ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እግር ኳስ ፌደሬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወልደሚካኤል መስቀሌ፤ በክልሉ ሲደረግ የነበረው ውድድር የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና አንድነትን ማጠናከሩን አስረድተው፤ በውድድሩን ከ1ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ክለቦች ክልሉን ወክለው በአገር አቀፉ የክለቦች ሻምፒዮና ከ28/10/2017 – 27/11/2017 እንደሚሳተፉም ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ በአዲሱ የውድድር ዓመት 2ኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል
ጄሚ ቫርዲ ወደ ጣሊያን ሴሪኣ ሊያቀና ነው