በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ አስተዳደር ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
የላስካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋለም ላቀዉ ግብርን በሙሉ ፍላጎት መክፈል የሀገር ፍቅር ማሳያና የሰለጠነ ዜጋ መገለጫ ነዉ ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በ2017 በጀት አመት ከመደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ 71 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ባለፉት 11 ወራት 70 ሚሊዮን 171 ሺህ 298 ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል።
የ2017 ግብር ከሐምሌ አንድ ጀምሮ በንቅናቄ ለመሰብሰብ መረጃ የማጣራት እና የትመና ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አቶ ተስፋለም ገልፀዋል።
ግብር ከፋዮችም ከወዲሁ በመዘጋጀት ያለባቸውን ግብር በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል የዜግነት ግዴታቸዉን እንዲወጡም አሳስበዋል።
ካነጋገርናቸው ግብር ከፋዮች መካከል አቶ ተፈራ ፈለቀ ፣አቶ ኢያሱ ዶታና አቶ በላይ ባርኮ እንዳሉት ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታ መሆኑን ገልጸው የ2017 ግብር በወቅቱ ከፍለው ለማጠናቀቅ መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል።
ግብር ለመክፈል ቀድሞ መዘጋጀት ከአላስፈላጊ ቅጣትና መጉላላት እንደሚታደግ የተናገሩት ግብር ከፋዮች ገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤትም የግብር ከፋዮችን ግንዛቤ ለማሳደግ እየሰራ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል።
በላስካ ከተማ አስተዳደር ከ1ሺህ 1 መቶ በላይ ደረጃ “ሐ” ከ50 በላይ ደረጃ “ለ” እና ከ70 በላይ ደረጃ “ሀ”ግብር ከፋዮች መኖራቸዉን የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
ዘጋቢ ፡መንግስቱ ታሪኩ-ከሳዉላ ጣቢያችን
More Stories
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ማህበረሰቡን ከቱርካና ሐይቅና ከኦሞ ወንዝ ሙላት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በስፍራው በመገኘት ተመለከቱ
የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በየደረጃዉ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ አስታወቀ
የህዳሴው ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ያሳኩት የጋራ ድል መሆኑን የጨታ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ