የቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር አደገ አለሙ በክልሉ ማዕከላዊና ሰሜን ሲዳማ ዞኖች ዳሌ እና ሸበዲኖ ወረዳ በዶሮ ልማት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ከግብርና ሚንስቴር ከመጡ ከፍተኛ ባለሞያዎች ጋር ምልከታ አድርገዋል።
በመስክ ምልከታ ወቅት በጤዲቻና መሲንቾ ሜዳ ቀበሌ ዶሮን ከራስ ምግብነት ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ጭምር አርሶ አደሮች ምርታማነታቸውን እያረጋገጡ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ካለፉት ሦስት ዓመት ወዲህ የሌማት ቱሩፋት መርሐ ግብር በክልሉ አበረታች ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቀሱት ም/የቢሮው ሃላፊው አምራቹን ሐይል ከተጠቃሚው ጋር የማገናኘት ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
እንደ ሃገር ያጋጠመውን የመኖ አቅርቦት እጥረትን ለመቀነስ ክልሉ ከግብርና ሚንስቴር ጋር ተነጋግሮ ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ: አርሶ አደሩ በቤት ውስጥ የሚመገበውን የተራረፈ ምግብ በጥንቃቄ ለዶሮ መኖነት መጠቀም እንዲችል ጠይቀዋል።
በግብርና ሚንስቴር የዶሮ ልማት ሃብት ዴስክ ሃላፊ ዮናታን ዘውዴ በበኩላቸው የዶሮን ምርታማነት ለመጨመር የተለያዩ የዶሮ አረባብ ዘዴዎችን በመጠቀም በክልሉ የተሰራው ተግባር ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።
በሚንስቴር መስርያ ቤቱ የተያዘውን “አርሶ አደሩን የሚመስል መንደር” የመፍጠር ዕቅድ ዕውን ያደረገ እንቅስቃሴ መመልከት መቻላቸውንም አንስተዋል።
የእንስሳት መኖ አቅርቦትን ጨምሮ እንቁላል ጣይና ቄብ ዶሮዎችን አሳድጎ ለአርቢዎች የማከፋፈል ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት በሐዋሳ ሱፐር ኦቫ አግሮ ቴክ የእንስሳት ሐኪም ዶ/ር ፈቃዱ ኡርጋ የህብረተሰቡን የእንቁላል ፍላጎት ለማርካት መሰራቱን ገልጸዋል።
አርሶ አደሮች በበኩላቸው ምርታማነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ችግር እንዲቀረፍ ሲሉም ጠይቀዋል።
ዘጋቢ :በምህረተአብ እስራኤል

More Stories
አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ ለ9ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 121 ተማሪዎችን አስመረቀ
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ