በከተማ አስተዳደሩ ከአንድ መቶ ሺ በላይ የቡና ችግኞችን በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱን የሆሳዕና የከተማ አስተዳደሩ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡
የቡና ምርት የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ የግብርና ምርት ዘርፎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ በመሆኑ በዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ስመለሆኑም ነው የጠቆሙት።
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሀድያ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሃብታሙ ታደሰ
የቡና ልማት ተግባር የአርሶአደሩን ኑሮ ከመቀየሩም ባሻገር የሀገርን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የተጀመረው የኩታ ገጠም የቡና ችግኝ ተከላ ለሌሎች አካባቢዎችን ምርጥ ተሞክሮ በመሆኑ ይህንን እንደመነሻ በመውሰድ የኤክስቴንሽን ስራው በተገቢው እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በሀድያ ዞን ዘንድሮ 7 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ሀብታሙ በከተማ አስተዳደሩ የተጀመረው ተግባርም የዚሁ አንዱ አካል እንደሆነ አብራርተዋል።
በመርሃ ግብሩ ተገኝተው የቡና ተከላውን ያስጀመሩት ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ በከተማ አስተዳደሩ በግብርና ዘርፍ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው የቡና ችግኝን በአዲሰ መልክ ለማልማት መታሰቡ በአከባቢውና በአገሪቱ ላይ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አክለዋል።
የቡና ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የተከናወንበት ማሳ ባለቤት አርሶ አደር ጌታቸው ኑሬቦ ካላቸው የእርሻ መሬት በአንድ ሄክታሩ ማሳ የቡና ችግኝ መትከላቸውንም ተናግረዋል።
በቀጣይም የተተከሉትን የቡና ችግኞች በመንከባከብና በማስፋፋት በምርቱ ኑሯቸውን ለመቀየር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:ኤርጡሜ ዳንኤል-ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-