ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ግብፅን ትገጥማለች
በሞሮኮ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ቶታል ኢነርጂስ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት መካሄድ ይጀምራል።
በምድብ አንድ የተደለደለው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ከግብፅ ጋር ዛሬ ያከናውናል።
ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በመሐመድ ስድስተኛ ኮምፕሌክስ ይደረጋል።
ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተሻገሩት ቀይ ቀበሮዎቹ ለጨዋታው ሙሉ ቢጫ መለያ የሚጠቀሙ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ከማክስ ዶውማን ጋር መስራት ትልቅ ደስታ ነው” ሚኬል አርቴታ
ስፖርት ፍቅርን፣ ሰላምን እና አንድነትን ለማምጣት ወሳኝ ነው – የቡርጂ ዞን አስተዳደር
“እናቴ ሆይ ደውይልኝ!”