በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
ይህንን የተናገሩት በክልሉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በተከናወነው የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡኝ ቅስቀሳና ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ነው።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የብልጽግና ፓርቲ ካለፉት ስምንት ዓመታት ጀምሮ የተረሱ አካባቢዎችን በፖለቲካና በልማት ዘርፍ የእኩል ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እያስቻለ ይገኛል።
የዞኑ ነዋሪዎች ያደሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከለውጡ ወዲህ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ዞኑ በገጸ ምድርና በከርሰ ምድር ሀብት የበለጸገ በመሆኑ በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ በተከናወነው ተግባር ተጨባጭ ውጤት እየታየ መጥቷል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ክልሉ ክልል ሆኖ ከተደራጀ ወዲህ ለዞኑ ልዩ ድጋፍ በማድረግ በሰላምና ጸጥታ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርናና በእንስሳት ሕክምና ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች በትኩረት እየተሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በዞኑ የሚገኙ ብሔረሰቦች በፖለቲካ ዘርፍ ውክልና እንዲኖራቸው ለማድረግና ክልላዊ አንድነትና አብሮነትን ለመፍጠር የተሻለ ተግባር መከናወኑንም ገልጸዋል።
ዞኑ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የልማት ዘርፎች ተጠቃሚ ለመሆን ያስቻለው የብልጽግና ፓርቲ የመደመር እሳቤ ላይ በመመርኮዝ በመሆኑ ምርጫቸው የብልጽግና ፓርቲ እንዲሆንም ገልጸዋል።
ለዞኑ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የክልሉ መንግሥት ድጋፋዊ ክትትል ወሣኝ በመሆኑ አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉም አሳስበዋል።
የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው እንደገለፁት፤ ሕዝቡን በሁለተናዊ የልማት ዘርፍ የእኩልነት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እያከናወነ የሚገኘው ተግባር በሕዝቡ በመውደዱ ተመራጭ በመሆን እያበበ የሚገኝ ፓርቲ ነው።
የለውጡ መንግሥት የተደበቁ አጀንዳዎችን በመግለጥ ለአገሪቱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የልማት ዘርፎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ መሆኑንም ተናግረዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የሕዝቡን ሁለተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረግጡ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማስጀመር ብቻ ሳይሆን ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ሥራም የሚሠራ ፓርቲ መሆኑን አስረድተዋል።
የፖለቲካ መረጋጋትን እውን ለማድረግ በፖለቲካ ዘርፍ የአፍሪካ ተምሳሌታዊ አገር ለመሆን እየሠራ በመሆኑ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን ገልፀዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የሚያስችል ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።
እንደአገር የተጀመረውን ልማት ለማስቀጠል የብልጽግና ፓርቲን እንዲመረጡም አሳስበዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ፤ የብልጽግና ፓርቲ ለትውልድ የሚሠራ ፓርቲ በመሆኑ የዞኑን ነዋሪዎች በልማት ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያደርግ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።
ዞኑ ለአገር ኢኮኖሚ ሊያበረክት የሚችል የማዕድን ሀብትና የግብርና ዘርፍ ልማት ላይ ሊለማ የሚችል ሰፊ ማሣ ባለቤት በመሆኑ የዞኑ የመዋቅር ጥያቄ እንዲፈታ ያስችለ ፓርቲ በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።
የጀሙ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሽፈራው ማናባ እንደገለፁት፤ በብልጽግና ፓርቲ የከተማ ነዋሪዎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እየተመለሱ ይገኛሉ።
በመሆኑም በከተማዋ በበጀት ዓመቱ ከ8 መቶ 50 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል
ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከቦንጋ ማስተባበሪያ

More Stories
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል
በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት እየተስተዋለ ያለውን ድህነት እና የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ያበረከተው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑ ተገለጸ