የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከ103 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተገነባው የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ህንጻ የምርቃት ስነስርአት እየተከናወነ ነው።

‎ከ103 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ህንጻ በውስጡ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ 53 ክፍሎችና እስከ 500 ሰው መያዝ የሚችል የስብሰባ አዳራሽም ያካተተ ነው።

‎በተጨማሪም ደረጃውን የጠበቀ ባለ 4 ኮከብ ሆቴል የህንፃ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርአት እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሀ ግብሩ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና እና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ኑርዬ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊና የከተማና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የከተማ የስራ ሀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ መላኩ ንማኒ – ከወልቂጤ ጣቢችን