ሀዋሳ፡ ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአይቻልምን ትርክት የሰበረ የኢትዮጵያዊነት የጋራ ፕሮጀክት መሆኑን የጎፋ ዞን አስተዳደር ገለፀ፡፡
በጎፋ ዞን ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ለግድቡ ግንባታ ሀብት ለመሰብሰብ መታቀዱ ተመላክቷል።
የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ አቶ ምናሴ ኤሊያስ፥ ግድቡ የብሄራዊ ኩራታችን መገለጫ ነው ያሉት ኃላፊው፥ በዞኑ ከ30 ሚሊየን ብር ለግድቡ ግንባታ ሀብት ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከአሁን 60 በመቶ መሰብሰቡን ጠቅሰው በአንድ ወር ቆይታው ቀሪውን ለማጠናቀቅ መታቀዱን ገልጸዋል።
በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መኮንን ቶንቼ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የአይቻልምን ትርክት የሰበረ የኢትዮጵያዊነት የጋራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው የግድቡ ዋንጫ በዞኑ ለአንድ ወር በሚኖረው ቆይታ የተጠናከረ ድጋፍ በማድረግ የጀመርነውን ግድባችንን በጋራ ለመጨረስ መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ አቶ መንግሥቱ ማጃ በመጠናቀቅ ላይ ለሚገኘው ግድባችን ዋንጫውን የተረከበው የጎፋ ዞን የተሳካ አስተዋጽኦ ለማበርከት መዘጋጀቱ የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ወደ ጎፋ ዞን ሲገባ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች አቀባበል አድርገዋል።
በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ የዞኑ ነዋሪዎችም የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በ6 ወራት ውስጥ ሊመዘበር የነበረ ከ156 ሚሊየን 560ሺህ ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የጉራጌ ክትፎ ባህልና እውቀትን በዩኒስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ እንደሚገኝ የኢፌዲሪ ቅርስ ባለስልጣን ገለፀ
በክልሉ ያሉ ብሔረሰቦችን ባህል ወደፊት በማውጣት የአካባቢውን ሰላምና ልማት ለማስቀጠል በትኩረት መስራት እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ተናገሩ