ሀዋሳ፡ ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኣሪ ዞን ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከወርልድ ቪዥን ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከወረዳና ከተማ አሰተዳደር የሀይማኖት ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት መደረክ ተካሄዷል ።
የውይይት መድረኩ በአባቶች ፀሎትና ምርቃት ነው የተጀመረው፡፡
በውይይት መደረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የኣሪ ዞን ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ሃላፊ አቶ ማታዶ በርቢ፥ የሐይማኖት ተቋማት በህዝቡ መሀል ሠላምና አብሮነት እንዲሰፍን ላደረጉት አሰተዋጽኦ ምስጋና አቅረበው ቀጣይም የተለመደው ተግባር እንዲጠናከር ጥሪ አቀረበዋል ።
በውይይት መደረኩ የ2017 ዓም የሀይማኖት ተቋማት ፎረም በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የተሠሩ ሥራዎች ሪፖሪት የቀረበ ሲሆን፥ የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በሰነዱ መነሻ ከተሳታፍዎች መካከል አቶ ኡመርዲን ግርማ አቶ ካሳሁን ጠቃይና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት የተሠሩ ስራዎች ጥሩ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይ የሀይማኖት ፎረሙ በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነትና መተሳሰብ በማስረፅ በኩል ትኩረት እንድሰጥበት ጠይቀዋል።
የኣሪ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ በበኩላቸው፥ የሀይማኖት ተቋማት ፎረም የህዝብ መሪ እንደመሆኑ የህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ባህልንና ሥርዓትን በተከተለ ሁሉን እኩል በማሳተፍ መምራት የሚገባው ጠቁመዋል፡፡
ኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ፥ ልማትና ዴሞክራሲ የሚረጋገጠው በሠላም መሆኑ በቀጣይም ለሠላም የሚያበረክቱትን አስተዋጾኦ እንዲያጠናክሩና ለአከባቢና ለሀገር እንዲተጉ ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፡ ደፋሩ ስፍታዬ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እያስመዘገበች ላለችው የዕድገት ጉዞ ቀጣይነት የትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለትምህርት ጥራት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ሲል የጋሞ ዞን አስተዳደር አሳሰበ
በትምህርት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን አጽንቶ ማስቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ገለፁ
በኮንታ ዞን ጳጉሜን 1 – የጽናት ቀን በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል