የሀገሪቱን ቦክስ ስፖርት ለማሳደግ የቀድሞ ቦክሰኞችና ሌሎችም አስተዋጽዋቸውን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

የሀገሪቱን ቦክስ ስፖርት ለማሳደግ የቀድሞ ቦክሰኞችና ሌሎችም አስተዋጽዋቸውን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

ሀዋሳ፡ ግንቦት 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀገሪቱን ቦክስ ስፖርት ለማሳደግ የቀድሞ ቦክሰኞችና ሌሎችም አስተዋጽዋቸውን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ የትግራይ ክልል ቦክስ ፌዴሬሸን ፀሐፊ አቶ ቶማስ ካሳ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ዓለም አቀፍ የቦክስ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ካሳሁን በቀለ መቀሌ ለሚገኙ ታዳጊ ቦክሰኞች የተግባር ስልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ፌዴሬሽኑ ገልጿል፡፡

የትግራይ ክልል ቦክስ ፌዴሬሸን ጸሐፊ አቶ ቶማስ ካሳ በክልሉ መቀሌን ጨምሮ አላማጣ፣ ሽሬ እና አዲግራት የቦክስ ስፖርት አሁን ላይ እንደ አዲስ እየተጀመረ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢንስትራክተር ካሳሁን በቀለ በራስ ተነሳሸነት የክልሉ ስፖርት ለማነቃቃት የተግባር ስልጠና መስጠቱ እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፍ በማበርከቱ አመስግነዋል፡፡

ሌሎችም መስል በጎ ተግባር በማከናወን የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን የቦክስ ስፖርት ለማሳደግ የበኩላቸው ድርሻ እንዲወጡ የትግራይ ክልል ቦክስ ፌዴሬሸን ጸሐፊ አቶ ቶማስ ጠይቋል፡፡

ኢንስትራክተር ካሳሁን በቀል በበኩሉ ባለፉት ዓመታት በክልሉ በተፈጠረው አለመረጋጋት የተቀዛቀዘውን የቦክስ ስፖርት ለማነቃቃት ያካበተውን ዓለም አቀፍ ዕውቀትና ተሞክሮውን ለታዳጊ ቦክሰኞች ለማካፈል እንደተነሳሳ ገልጿል፡፡

በቀጣይም በሀገሪቱ ሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ ታዳጊ ቦክሰኞች ስልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጧል፡፡

ኢንስትራክተር ካሳሁን በቀለ ከዚህ ቀደም ለአብጂም ቦክስ ማሰልጠኛ፣ ለአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽንና ለኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን በሚሊዮን የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ ጫካ – ከቦንጋ ጣቢያችን