በቴክኖሎጂ የታገዘ መንግሥት የግዥ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ የሀብት ብክነትን መቀነስ ይገባል – ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የኢፌዲሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን በመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥረዓት አተገባበር ዙሪያ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቦንጋ ከተማ ውይይት እያደረገ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ በቴክኖሎጂ የታገዘ መንግሥት የግዥ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ የሀብት ብክነትን መቀነስ ይገባል ብለዋል።
የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ውስን የኾነውን የህዝብና የመንግሥት ሀብት በተገቢው ከማስተዳደር ባለፈው በግዥ ስርዓት ሂደት ውስጥ ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስረዓት እንደሆነ ገልጸዋል።
በክልሉ የሚከናወኑ የመንግሥት የንብረትና የአግልግሎት ግዥዎችን በቴክኖሎጂ በተጋዘ መልኩ በማሳለጥ የጊዜና የሀብት ብክነትን ለመቀነስ የክልሉ መንግሥት በቁርጠኝነት አንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።
በመድረኩ የተገኙት የኢፌዴሪ የግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት (ኢጂፒ) አስፈላጊነትና ጠቀሜታዎች እንዲሁም ዝርዝር አፈጻጸም ዙሪያ ገለጻ እየሰጡ ይገኛል።
ምንጭ፡ የክልሉ መንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
More Stories
በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ በግብርናው ዘርፍ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ወጣቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገለጹ
በምርጥ ዘር ብዜት ሥራ አርሶ አደሩን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው – የኣሪ ዞን አስተዳደር
በክልሉ የሚመረቱ የግብርና ውጤቶች ላይ እሴት ጨምሮ ለማገበያየት የሚያስችል ኢንዱስትሪ ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ