በዳውሮ ዞን በሎማ ቦሣ ወረዳ የወባ ወረርሽን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት እየተካደ ነው
የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ብርሃኑ ድግሦ በወረዳወ በሚገኙ 27 ቀበሌያት መከላከልን መሠረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ እያንዳንዱ ነዋሪ ንጽሁ ሽንት ቤትን እንዲኖረው በማድረግ ፣ደርቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻ በአግባቡ የማስወገድ ሥራ ስርዓት እንዲኖር ማድረግ መቻሉን ገልጿል።
በወባ ትንኝ መራቢያ አከባቢዎች የቤት ለቤት ኬሚካል ርጭት ከማስመጀመር ባለፈ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማዳፈንና የማፋሰስ ሥራዎች መከናወኑን አስረድተዋል። ኬሚካል ርጭት የወባ በሽታ ወረርሽኝ ከፍተኛ በሆነባቸው በ12 ቀበሌያት እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡም ለተከታታይ 6 ወራት ኬሚካል በተረጨ ቤት ላይ ቀለም ይሁን ተመሳሳይ ነገር ባለመቀባት እንዲሁም አጎበር በተገቢው በመጠቀም የውሃ ማፋሰሻዎች በመስራት ራሳቸውን ከወረርሽኙ መጠበቅ እንደሚገባም አመላክተዋል።
አዘጋጅ: አንዱዓለም ኡማ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
በኮሬ ዞን የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከል የተጀመረው የክትባት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የወላይታ ዞን አስተዳደር ገለጸ
በቶ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ የማህበረሰቡ እንግልት መቀነሱ ተገለፀ