ህገ-ወጥ የምርት ግብይት እና ዝውውርን ለመከላከል የንግድ ሥርዓቱን ማዘመን እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለጸ
ቢሮው ከክልሉ የምግብ ሥርዓተ ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች የግንዛቤና አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና በሚዛን አማን ከተማ ሠጥቷል።
የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ከክልሉ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ የግብርና ምርቶች ግብይት እና ዝውውር እንዲሁም በንግድ ፍቃድና ምዝገባ ዙሪያ በክልሉ ከሁሉም ዞኖች ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በሚዛን አማን ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።
በዕለቱም የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ እንደገለጹት፤ ስልጠናው በተለይ የኤክስፖርት ምርቶችን እንዴት መምራት እንደሚቻልና ግብይቱን ማዘመን በሚቻልበት ዙሪያ ትኩረት ይደረጋል፡፡
አክለውም የንግድ ቀጠና ትስስር በኢትዮጵያ ያለውን የንግድ ሥርዓት ለማዘመን እየሠራ ይገኛል፤ ይህን ተከትሎ ክልሉም በዘርፉ ላይ ያተኮረ ስልጠና ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የንግድ ምዝገባ ወይም የኢትሬድ ፅንሰ ሀሳብ እንደ ሀገር ከተጀመረ ሁለት ዓመታት ማስቆጠሩን የገለፁት አቶ ተመስገን፤ በእነዚህ ዓመታት በክልሉ ካሉት ከ62 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ከ22 ሺህ በላይ የሚሆኑት ኢትሬድ በመመዝገብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በቢሮው የንግድ አሠራርና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ አምዴ ፋሪስ በበኩላቸው፤ ህገ-ወጥ ንግድን መከላከል ሚቻለው የንግድ ሥርዓቱን በማዘመን፣ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበርና በንግዱ መዋቅር የሚሠሩ ባለሙያዎች አቅም ሲጎለብት ነው ብለዋል።
ከሠልጣኝ ባለሙያዎች መካከል ሩት ተፈራ ከኮንታ ዞን፣ መስፍን በፍቃዱ ከከፋ ዞን፣ ጥሩዓለም ይልማ ከምዕራብ ኦሞ በሰጡት አስተያየት በተለይ ህገ-ወጥ የኤክስፖርት ምርቶችን ግብይት መከላከል ስላልው ፋይዳና ዲጂታላይዜሽን ወይም ኢትሬድ ለንግዱ ማህበረሠብ ስለሚያበረክተው አስተዋጽኦ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ ሰለሞን ፈጠነ – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል