የኢድ አልፈጥር በዓል በዋናነት የተቸገሩትን በመርዳት ያለንን ለሌሎች በማካፈል የምናከብረው በዓል ነው – የኮሬ ዞን እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት
ሀዋሳ፡ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢድ አልፈጥር በዓል በዋናነት የተቸገሩትን በመርዳት ያለንን ለሌሎች በማካፈል የምናከብረው በዓል ነው ሲል የኮሬ ዞን እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
1ሺህ 446ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ማድረጉን የኮሬ ዞን እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የኢድ በዓል በዞኑ ስር ከሚገኙ መዋቅሮች ለመጡ አስተባባሪዎች ገለጻ መስጠቱን የኮሬ ዞን እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል።
የኮሬ ዞን እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ሼህ አቡዱራሃማን ሱሌማን ከፊታችን ለ1ሺህ 446ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢድ በዓል አስመልክተው በሰጡት ገለጻ፤ እንደ ሀይማኖት ተቋማቸው አስተምህሮ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን አስረድተዋል።
በዓሉ ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች በሸሪዐ ህግ መሰረት ዘካ ቱልማ ወይም በግለሰብ ደረጃ ሁለት ኪሎ ከግማሽ እህል በማዋጣት የተቸገሩትን በመርዳትና በመደጋገፍ እንዲያከብሩ መመሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
ከእምነቱ ተከታዮች የተሰበሰበውን ገንዘብ በበዓሉ ዕለት ለተቸገሩት እንዲያከፋፍሉ ለሁለቱ መዋቅሮች መስጠታቸውንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
የዞኑ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሼህ ሱልጣን አብዱራህማን በበኩላቸው፤ በዓሉ በዋናነት የተቸገሩትን በመርዳት ያለንን ለሌሎች በማካፈል የምናከብረው በዓል ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የጎርካ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ ሼህ አብዱርቃድር አደን፤ በወረዳ ደረጃ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል።
የእመነቱ ተከታዮች በበኩላቸው፤ በሀይማኖታቸው ስርዓት መሰረት ለአንድ ወር ሲጾሙ ቆይተው አሁን ላይ የኢድ በዓሉን ለማክበር በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኢድ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም ለ1ሺህ 446ኛ ጊዜ ይከበራል።
ዘጋቢ: ተሾመ ጸጋዬ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የማህበረሰቡን አንድነት፣ ሠላምና ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ባህላዊ እሴቶችን ጠብቆ በማቆየት ለትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
በክህሎት ፣ በቴክኖሎጂና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ውድድር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ
በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ