የፕሪሚየርሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪዎች ማንቼስተር ሲቲ እና አርሰናል ፍልሚያቸውን ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ፡፡
በጨዋታው መድፈኞቹ ከተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት እና ከ19 ዓመት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ለሦስት ዋንጫ የሚፎካከሩት ውሃ ሰማያዊዎቹ በአንፃሩ ትኩረታቸው የሻምፒዮንስ ሊጉ ዋንጫ ላይ ቢሆንም ከአርሰናል ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት በማጥበብ የሊጉን ዋንጫ በተከታታይ ለማንሳት ይጫወታሉ፡፡
የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ÷ ‘‘የምሽቱ ጨዋታ የዋንጫ አሸናፊነታችንን አይወስንም ፤ ነገር ግን በሊጉ በመሪነት ለመቆየት ያስችለናል’’ ብለዋል፡፡
ተጫዋቾቼ በጥሩ ስነ ልቦና ላይ ይገኛሉ ያለው አርቴታ ፥ የቡድናችንን ጥንካሬ በዛሬ ምሽቱ ጨዋታ እናሳያለን ሲል ተናግሯል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሚደረገው ጨዋታ በአርሰናል በኩል ተከላካዩ ዊሊያም ሳሊባ በጉዳት ምክንያት ከጫዋታ ውጭ ሲሆን ፥ የመሀል ክፍሉ ሞተር ግራናይት ዣካ የመሰለፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡
በሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪው ኤርሊንግ ሃላንድ ፊታውራሪነት የሚመሩት ውሃ ሰማያዊዎቹ ባንፃሩ የናታን አኬን አገልግሎት የማያገኙ ሲሆን ፥ እሱን በመተካት ማኑኤል አካንጂ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
More Stories
ሮድሪጎ ቤንታንኩር ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ታገደ
በቀቤና ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የማስ ስፖርት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ