በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና መስፍን ታፈሰ፣ ሮቤል ተክለሚካኤል፣ አንተነህ ተፈራ እና አማኑኤል ዮሐንስ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የድሬዳዋ ጎል ያሲን ጀማል አስቆጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 30 በማድረስ ከሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ ጋር እኩል 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡
ምሽት 12፡00 ላይ ባሕርዳር ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
የባሕር ዳር ከተማን ጎሎች ሃብታሙ ታደሰ እና አደም አባስ እንዲሁም የኢትዮጵያ መድንን ሳይመን ፒተር እና ሀቢብ ከማል አስቆጥረዋል፡፡

More Stories
ቼልሲ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን አስፈረመ
ማንቼስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ድሉን ፍለጋ ከኢፕስዊች ጋር ይፋጠጣል
ሚካኤል አርቴታ ለአርሰናል 250ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ሊመሩ ነው