የማህበረሰቡን የመልማት ጥያቄዎች ለመመለስ አስቻይ የሆኑ ስራዎች ላይ ማተኮር ከአመራሩ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
ሀዋሳ: መጋቢት 06/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሚቀጥሉት ሶስት ወራት የማህበረሰቡን የመልማት ጥያቄዎች ለመመለስ አስቻይ የሆኑ ስራዎች ላይ ማተኮር ከአመራሩ እንደሚጠበቅ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ አሳሰቡ።
በክልሉ የቀጣይ የ90 ቀናት የመንግስትና የፓርቲ የስራ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።
ከመጋቢት 1 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም በመንግስትና በፓርቲ መሳካት አለባቸው ተብለው የታለሙ ዕቅዶችን ወደ መሬት ማውረድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እተወያዩ ያሉት።
በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ዕቅዱ አላማው እንዲያሳካ አመራሩ በጥብቅ ዲሲፕሊን መከታተል ይኖርበታል ብለዋል።
ባለፋት ጊዜያት ፈተናዎችን በመቋቋም ውጤት እንደመጣው ሁሉ ዕቅዱን አሳክቶ የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ለመመለስ አንድነት ላይ ቆሞ መስራት ይጠበቃል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ
More Stories
በኩታ ገጠም እየተከናወነ ባለው የቡና እና ሌሎች ፍራፍሬ ምርት ተከላ ኢኒሼቲቭ የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት በአጭር ጊዜ እያሳደገ መምጣቱን በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች እስከአሁን ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ህብረት ስራ ማህበራት በተደራጁበት ዓላማ ለአባሎቻቸው የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በጠንካራ አደረጃጀትና ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት ሊደገፉ እንደሚገባ ተመላከተ