የጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 05/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃግብር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ።
የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አበበ አማኔ ምክር ቤቶች የህዝብን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ፣ የአስፈፃሚውን ተግባራትን መገምገምና አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንዳርጌ አራታ በግብርናው ዘርፍ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት ቢኖርም አርሶአደሩ ተክኖሎጂ የመጠቀም ችግሮች በመኖሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከግንዛቤ ጀምሮ ብዙ ስራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
በአከባቢና ደን ጥበቃ ስራዎች ላይ ውስንነቶች መኖር፣ በሻይና ቅመማ ቅመም፣ በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ዝቅተኛ አፈፃፀም መኖሩን አንስተው በቀጣይ ትኩረት የሚሹት ጉዳዮች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በማህበራዊ ዘርፍ 904 አባወራና እማወራዎች በጎርፍና በመሬት መንሸራተት አደጋ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፎች ማድረጋቸውን ጠቁመው፥ አሁንም የከፋ አደጋ የደረሰባችውን ወገኖች ለይቶ ድጋፎች እየተደረጉ መሆናቸውን አንስተዋል።
በወረዳው ከ11 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በላይ የኦዲት ግኝት ቢኖርም የህዝብና የመንግስት ገንዘብ አመላለስ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ 129 ሄክታር መሬት ለወጣቶች ለማስተላለፍ ታቅዶ 78 ሄክታር መሬት ማስተላለፍ መቻሉንና 20 ሄክታር መሬት በትራክተር መታረሱን አቶ አንዳርጌ አስረድተዋል።
የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው በሰጡት ሀሳብና አስተያየት የኦዲት ገንዘብ አመላለስ ውስንነቶች ለመፍታት በሰው እጅ የሚገኙ ገንዘቦች በአዋጁ መሠረት በአፋጣኝ የማስመለስ ስራ ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበትም አፅንኦት ሰጥተዋል።
አክለውም በትምህርት ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን የተማሪ ወላጅ፣ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስበው ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።
የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ድልነሳው ዲዶ ያለፉትነ ስድስት ወራት አፈፃፀም ቀርቦ ከምክርቤት አባላት ሀሳብና አስተያየት ሰጥተዋል።
የምክር ቤት አባላት በሰጡት ሀሳብና አስተያየት የኦዲት ገንዘብ አመላለስ ውስንነቶች ለመፍታት በሰው እጅ የሚገኙ ገንዘቦች በአዋጁ መሠረት በአፋጣኝ የማስመለስ ስራ ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበትም አፅንኦት ሰጥተዋል።
አክለውም በትምህርት ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን የተማሪ ወላጅ፣ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስበው ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።
ከደምባ ጎፋ ወረዳ ወደ ሳውላ ከተማ አስተዳደር የታቀፉ ቀበሌያትን ምክር ቤቱ ለሳውላ ከተማ ያስረከበ ሲሆን የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ኢያሱ አዲሱ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማሳደግ እንደ ሀገር ለተጀመረው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ለውጥ የማይተካ ሚና እንዳለው ተገለፀ
ሠላምን በማፅናት ስራ የመንግስታት ግንኙነት እና ሃገረ መንግስት ግንባታ ወሰኝ መሆኑ ተገለጸ
ሴቶች በእውቀትና በሀሳብ በመደጋገፍ ራሳቸውን ለማብቃት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቆመ