ሠላምን በማፅናት ስራ የመንግስታት ግንኙነት እና ሃገረ መንግስት ግንባታ ወሰኝ መሆኑ ተገለጸ

ሠላምን በማፅናት ስራ የመንግስታት ግንኙነት እና ሃገረ መንግስት ግንባታ ወሰኝ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ መጋቢት 05/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሠላምን በማፅናት ስራ የመንግስታት ግንኙነት እና ሃገረ መንግስት ግንባታ ወሰኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ መቱ አኩ ገለፁ።

የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት የሀገረ-መንግስት ግንባታና የመንግስታት ግንኙነት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ በሚል ርዕስ የአሰልጣኞች ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።

የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መቱ አኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ላለው ሠላምን የማፅናት ስራ የመንግስታት ግንኙነትና ሃገረ-መንግስት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የሀገረ-መንግስት ግንባታ ከብሔረ-መንግስት ግንባታ ጋር አጣጥሞ ለመሄድ ነጠላ ትርክቶችን በማስቀረት አሰባሳቢ ትርክቶች በሚገባ እንዲሰርፁ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል።

ለዚህ ተግባር ደግሞ የባለድርሻ አካላት ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ሁለንተናዊ ሰላምን ለማምጣት የሀገር በቀል ዕውቀትን ከዘመናዊ ህጎች ጋር በማጣጣም በግጭት አፈታትና ሠላም ግንባታ ሂደት ላይ ሃገር በቀል ዕውቀትን በሰለጠነ መንገድ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በፌደራል ስርአት ውስጥ የመንግስታት ግንኙነት የሃገረ መንግስት ግንባታውን ለማሣለጥ ሆነ ሠላምን ለማፅናት የክልል መንግስት ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

ህግ አውጪ አካላት የወጡ ህጎች በተገቢው እየተፈፀሙ ስለመሆኑና ለሰላም ግንባታ ያላቸው አዎንታዊ ሚና በመገንዘብ መደገፍ እንደሚገባ ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል።

በአሰልጣኞች ስልጠና ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታን ጨምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቆጭቶ ገብረማሪያምን ጨምሮ ህግ አውጭ ህግ ተርጓሚና ህግ አስፈፃሚዎች በመሣተፍ ላይ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ አሣሣኸኝ – ከሚዛን ጣቢያችን