ምክር ቤቶች ለህዝብ የልማት ተጠቃሚነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 03/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ ተቋማት እንደ መሆናቸው መጠን ለህዝቡ የልማት ተጠቃሚነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አስታውቋል።
የዞኑ ምክር ቤት4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በጀሙ ከተማ እያካሄደ ነው።
ጉባኤውን በንግግር የከፍቱት የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ቢለልኝ ወልደሰንበት፥ ምክር ቤቶች በተሰጣቸው ስልጣን መሠረት ተግባራትን ለመገመገም እንዲሁም ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ መደበኛና አስቸካይ ጉባኤዎችን በመጥራት እንደሚሰራ ገልፀዋል።
ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ ተቋማት እንደ መሆናቸው መጠን ለህዝቡ የልማት ተጠቃሚነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናገረዋል።
በዞኑ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ እንደሀገር የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያን ልዕልና ከፍ የሚያደረጉ ውሳኔዎች በመወሰን ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት በመሆኑ ልዩ እንደሚያደረው ዋና አፈ ጉባኤው ገልፀዋል።
በሀገራችንም ሆነ በዞናችን በተነደፉ የመንግስት ፖሊሲዎችና አቅጣጫዎች መሠረት የማህበረሰቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የፍትህ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ በመሆኑ ይኸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የምክር ቤት አባላት የበኩላቸውን እንዲወጡ አቶ ቢለልኝ ተናገረዋል።
ምክር ቤቱ የ2017 ዓ.ም የአስፈፃፀም ላይ ውይይት በማደረግና ጉደለቶችን በማረም ለተሻለ ተግባርና ውጤታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚተጋበት ወቅት ነው ሲሉ ዋና አፈ ጉባኤው አፅንኦት ሰጥተዋል።
በጉባኤው የክልል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የዞንና የወረዳ እንዲሁም የከተማ አስተዳደር አመራሮች የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን ምክር ቤቱ በቆይታው የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅና የስራ መመሪያ በመስጠት እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መረሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
ዘጋቢ: አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች የህዝብን ጥያቄ ሊመልስ በሚችል መልኩ ሊሆን እንደሚገባ የሀዲያ ዞን ምክር ቤት አበላት ገለጹ
በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢሠራ ወረዳ ተገልጋዮች ተናገሩ
የጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ ተፈጥሯዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲቆይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አሰታወቀ