የሀዲያ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 24ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉበኤ ወ/ሮ እቴነሽ ሙሉጌታ በጉባኤው መክፈቻ እንዳሉት፤ በዞኑ በሁሉም መስኮች በ2017 የመጀመሪያ 6 ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል።
የዞኑ አስተዳደር ምክር የ6 ወር አፈጻጻም ሪፖርት ቀርቦ ከምክር ቤቱ አባላት በመሠረተ ልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶች እየተነሱ ነው።
በምክር ቤቱ የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ6 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት የሚቀርብ ሲሆን የተለያዩ ሹመቶችም ለምክር ቤቱ ቀርበው ይፀጽቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ: የአለቃል ደስታ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ