ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ
የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች፣ የህዝብ ክንፍና ባለድርሻ አካላት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል በፍቃዱ፤ ፍርድ ቤቶች ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ፎረም በማቋቋም በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
በ6 ወር አፈፃፀም የተመዘገቡ ውጤቶችን ይበልጥ በማጠናከር የተስተዋሉ ውስንነቶችን ለማረም በትጋትና በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አቶ ሳሙኤል በመግለፅ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ድጋፌ አገዜ፤ የፍትህ ተቋማት ጥምረት በመፍጠር በተከናወነው ተግባር በበጋ የቡና ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት የሚፈፀመውን የስርቆት ወንጀል መቀነስ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ የተሳተፉት የጌዴኦ ዞን የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ዘውዴ እና የዲላ ማረሚያ ተቋም ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ትዕግስት ሮቤ፤ በአፈፃፀሙ ሂደት የታዩ ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ የህዝቡን የፍትህ ጥያቄ ለመመለስ የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የተገኘው አንፃራዊ ሰላም የእርስ በርስ ግንኙነቶችን ከማጠናከር ባለፈ ለረጅም አመታት በፀጥታ ችግር ያለማውን የማዕድን ሀብት በመጠቀም የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በማጂ ወረዳ የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ
በአካል ጉዳተኝነት ተስፋ ባለመቁረጥ የተገኘ ስኬት
ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ