የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ ቤተ መንግስት ህንፃ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ
ክልሉ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የመስሪያ ቤት እጥረት ማጋጠሙን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ አዲሱ ፕሮጀክት ክልሉን ከከፍተኛ ወጪ ይታደጋል ብለዋል፡፡
በክልሉ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ከሚኖራቸው ውበትና ምቹ የስራ ቦታነት ባሻገር የሚፈጥሩት የስራ ዕድል እንደሚኖር ነው ዶ/ር እንደሻው በዚሁ ወቅት ያነሱት፡፡
የዛሬው የመሰረት ድንጋይ የማኖር መርሃ ግብር በክልሉ ሰባት ማዕከላት በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ ለተመሳሳይ የህንፃ ግንባታ ማስጀመሪያ ነው። የውስጥ ስራውን ሲጨምር እስከ 7 ቢሊየን ብር ይጠይቃል ነው የተባለው፡፡
የሃድያ ዞን አስተዳዳሪ ማቴዎስ አንዮ መሠል መሰረተ ልማት በአካባቢው መገንባቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታን ያስገኛል ብለዋል።
በሆሳና ከተማ የሚገነባው ቤተ መንግስት እና መሰብሰቢያ አዳራሽን በዋናነት ያካተተ ስለመሆኑ ግንባታውን የወሰደው ተቋራጭ ምክትል ስራ አስኪያጅ ዳንኤል ብርሃኑ ገልጸዋል።
ስራው በስድስት ወራት ጊዜ ቀንና ሌሊት ተሰርቶ ይጠናቀቃል ተብሏል።
ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ
More Stories
የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት የዘርፉን ተግባራት በተገቢው ለማሳካት ከምንጊዜውም በተሻለ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ