የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ የካቲት 29/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ።
ቢሮ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ተግባራት ዙሪያ ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ቦንጋ ከተማ ምክክር አካሂዷል።
በቢሮው የጸጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊና የወሳኝ ኩነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሰለሞን ደነቀ በተለያዩ አካባቢዎች የምዝገባ ስርዓቱ ያለበትን ደረጃ ለመገምገምና በምዝገባ ወቅት የሚፈጠሩ ክፍቶችን በአፋጣኝ ለመቅረፍ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።
በዚህም በክልሉ ባሉ 6 ዞኖች የድጋፍና ክትትል ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ኃላፊው አንስተዋል።
የምዝገባ ስርዓቱ እንዲሳለጥ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በምክክር መድረኩ በ6 ዞኖች የተደረጉ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ግብረ መልስ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በክልሉ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ መረጃ ቅበላ አቅርቦት አሪካይቭንግ ዳይሬክትሬት ዳይሬክተር አቶ በረከት መላኩ በበኩላቸው፥ የታዩ መልካም ልምዶችን ማጠናከርና ክፍቶች ላይ በቀጣይ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት የምዝገባ ስርዓቱ ውጤታማ እንዲሆን በባለቤትነት ስሜት እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።
ዘጋቢ፡ መቅደስ ታደሠ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች የህዝብን ጥያቄ ሊመልስ በሚችል መልኩ ሊሆን እንደሚገባ የሀዲያ ዞን ምክር ቤት አበላት ገለጹ
ምክር ቤቶች ለህዝብ የልማት ተጠቃሚነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ
በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢሠራ ወረዳ ተገልጋዮች ተናገሩ