የብርብር ከተማ አስተዳደር የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የብርብር ከተማ አስተዳደር የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

በጋሞ ዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምስ አዱማሱ በብርብር ከተማ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በከተማው የገቢዎች እና ፋይናንስ ጽ/ቤቶች እንዲሁም የማህበረሰብ መድሃኒት መደብር ሕንጻ ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አስቀምጠዋል።

የብርብር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብርሃም አይካ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በከተማው የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክረን ለነዋሪዎች የተመቸች ከተማ እንዲትሆን እንሰራለን ብለዋል።

በዞኑ በኩል የሚደረጉ ተከታታይ ድጋፎችን ያመሠገኑት ከንቲባው የነዋሪው የነቃ ተሣትፎ ሊጎላ እንደሚገባ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዶ/ር ደምስ አዱማሱ በከተማ አስተዳደሩ በ1.5 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባውን የሸማ መሥሪያ ማዕከል መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት በተለያዩ ምክንያቶች ከአዲስ አበባ ተፈናቅለው የመጡ ሥራ አጦችን በአንድ ማዕከል አሰባስቦ ሥራ በማስጀመሩ የከተማ አስተዳደሩን ካንቲባ አመስግነዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ለሥራ አጦች መቋቋሚያ ይሆን ዘንድ 500 መቶ ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመው፥ በቀጣይም ከተማዋን የልማት ኮሪደር ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበው፥ ለከተማው ልማት ሥራ የሚሆን 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን