የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የሴቶች ሚናን በተመለከተ የጋራ ውይይት በጂንካ ከተማ ተካሄደ
የኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ሴቶች ያልተሳተፉት ልማት ግቡን አይመታም ብለው በሁሉ አቀፍ የልማት ዘርፎች ሴቶች ተሳታፊ በመሆን ራሳቸውን በኢኮኖሚ እያበቁ እንደሆነና ይህም ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ዋና ሀላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነ፤ እንደሀገር ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል በልማት የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እንደሚሠራ አውስተዋል።
ሴቶች ለሠላምና አንድነት የሚያበረክቱት ሚና የጎላ መሆኑን የጠቀሱት ሀላፊዋ፤ በልማት ትሩፋት፣ በግብርና፣ በጤና እና መሰል ልማታዊ ሥራዎች ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በሀገራዊ ልማታዊ ተግባራት ሴቶች ያለ ፆታዊ ልዩነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሠራ በመሆኑ ሴቶች በራሳቸው በኩልም በዚህ ልክ በቁርጠኝነት መሥራት አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል ወ/ሮ እቴነሽ።
በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ በሴቶች አደረጃጀት ጠንክረው እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል።
የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሀላፊ ወ/ሪት ይመኙሻል ተፈሪ በበኩላቸው፤ እንደዞን በርካታ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተግባራት እየተከናወኑ እንዳሉ ጠቅሰዋል።
ይህ ይበልጥ በተሻለ መልኩ እንዲቀጥል በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን በሴቶች አደረጃጀት ተፈፃሚ እንዲሆኑ ይሠራል ብለዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል