ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ሁሉም በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ

ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ሁሉም በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ

መምሪያው የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።

በመድረኩ የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት ዴለቦ፤ መምሪያው የሰው ሀብትን በማነሳሳት ተቋማት በአደረጃጀት መሥራት እንዲችሉ፣ አቅም እንዲፈጥሩና የመንግስት አሰራሮች በተገቢው መንገድ መውረድ እንዲችሉ ከማድረግ ረገድ ከፍተኛ ተልዕኮ ያለው መሆኑን በመጠቆም በአገልግሎቱ ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ሁሉም በተሰማራበት ስራ መስክ በትጋት ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዞኑ መዋቅሮች ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው በመስራት ለተገልጋዩ እርካታ በመስራት በቀጣይ ለተሻለ ውጤት እንደሚሰሩም ኃላፊው ገልፀዋል።

የመምሪያው የልማት ዕቅድ ቡድን መሪ አቶ መኮንን ጠኮ፤ የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀርቡት ወቅት እንደገለፁት በአፈፃፀሙ በጠንካራ ጎን የተነሱትን ይበልጥ በማጠናከር በጉድለት የተለዩትን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል።

ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሚንኤል ይገዙና ዳዊት ያጋ፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለመግታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት አጥፊዎች ላይ አሰራርን ተከትሎ እርምጃ በመውሰድ ተገልጋዩ የሚያነሳውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን