በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻዎች ጋር ተካሄደ
ሀዋሳ፡ የካቲት 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለፀ።
መምሪያው በበጀት ዓመቱ በ8 ወራት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ ብር መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡
መምሪያው በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት በዞኑ ከሚገኙት መዋቅሮች ጋር የግብ ስምምነት በመፈራረም ወደ ተግባር መግባቱን የገለፁት የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌቱ ታምሩ ናቸው፡፡
በበጀት ዓመቱ 2 ቢሊዮን 818 ሚሊዮን 382 ሺህ 99 ብር ለመሰብሰብ በእቅድ ቢያዝም ነገር ግን በ8 ወራት ውስጥ 1 ቢሊዮን 343 ሺህ ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን አቶ ጌቱ አስታውቀዋል፡፡
በዞኑ በሚገኙ 8 ወረዳዎችና 5 የከተማ አስተዳደሮች ካሉት መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት ያልተሰበሰቡ ውዝፍና የዘመኑ ግብር በመለየት እስከ መጋቢት 15/2017 ዓ/ም ለመሰብሰብ አቅደው ወደ ተግባር መግባታቸውን የተናገሩት ኃላፊው፥ በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ህብረተሰቡ በግብይት ወቅት ደረሰኝ ጠይቆ እንዲቀበል ያስገነዘቡት አቶ ጌቱ ሁሉም ግብርን በወቅቱ በታማኝነት በመክፈል የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል እንደፈጠሩ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ
የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የሴቶች ሚናን በተመለከተ የጋራ ውይይት በጂንካ ከተማ ተካሄደ
ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ሁሉም በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ