በድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ሥርዓት ላይ የጤና ልማት ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ የካቲት 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ከድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ሥርዓት ጀምሮ በኢንስቲትዩቱ ያሉ ተያያዥ የጤና ልማት ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ እና በኢንስቲትዩቱ የሥርዓተ-ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ የተመራ ሉዑክ ጂንካ ከተማ ተገኝተው በኢንስቲትዩቱ ከቢሮ አደረጃጀት ጀምሮ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን ጉብኝትና ውይይት አድርገዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አጉኔ አሾሌ በንግግራቸው የጉብኝቱ ዋና አላማ ከድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ሥርዓት ጀምሮ ያሉ የጥናትና ምርምር፣ የመረጃ ሥርዓትና በክልሉ አርባምንጭ እና ጂንካ ላይ እየተገነቡ ያሉ የላብራቶሪ ማዕከላት ያሉበት የግንባታ ደረጃ ጉብኝት በማድረግ በአጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ የሚሰሩ የጤና ልማት ሥራዎችን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ እና በኢንስቲትዩቱ የሥርዓተ-ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ በጋራ እንደገለፁት ለጥናትና ምርምር ሥራ ከሰው ኃይል ጀምሮ ያሉ ችግሮችን በመፍታት ለማሰልጠንና በተለያዩ ጉዳዮች በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በተቋሙ ያሉ ችግሮችን በቅንጅት በመፍታት ውጤታማ ተግባራት ማከናወን የሚያስችል መግባባት የተፈጠረበት ውይይት እንደሆነ አመላክተዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ታሪክ፣ ባህሎችና ቅርሶችን ጠብቆ ማሳደግ ለቱሪዝም ልማትና ለህዝቦች ትስስር ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተጠቆመ
በኣሪ ወረዳ ያለው የመንገድ ችግር በማህበራዊ ህይወታቸው ሆነ በኢኮኖሚያቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑን የአከባቢው ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች ገለጹ
የእንሰት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከ69 ሺህ 1 መቶ በላይ ሄክታር ማሳ በእንሰት መሸፈን መቻሉን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዳዉሮ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ